عن سَعِيدِ بْنِ الْمُسَيَّبِ، عَنْ أَبِيهِ قَالَ:
لَمَّا حَضَرَتْ أَبَا طَالِبٍ الْوَفَاةُ، جَاءَهُ رَسُولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم فَوَجَدَ عِنْدَهُ أَبَا جَهْلٍ وَعَبْدَ اللهِ بْنَ أَبِي أُمَيَّةَ بْنِ الْمُغِيرَةِ، فَقَالَ: «أَيْ عَمِّ، قُلْ: لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، كَلِمَةً أُحَاجُّ لَكَ بِهَا عِنْدَ اللهِ»، فَقَالَ أَبُو جَهْلٍ وَعَبْدُ اللهِ بْنُ أَبِي أُمَيَّةَ: أَتَرْغَبُ عَنْ مِلَّةِ عَبْدِ الْمُطَّلِبِ، فَلَمْ يَزَلْ رَسُولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم يَعْرِضُهَا عَلَيْهِ، وَيُعِيدَانِهِ بِتِلْكَ الْمَقَالَةِ، حَتَّى قَالَ أَبُو طَالِبٍ آخِرَ مَا كَلَّمَهُمْ: عَلَى مِلَّةِ عَبْدِ الْمُطَّلِبِ، وَأَبَى أَنْ يَقُولَ: لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم: «وَاللهِ لَأَسْتَغْفِرَنَّ لَكَ مَا لَمْ أُنْهَ عَنْكَ»، فَأَنْزَلَ اللهُ: {مَا كَانَ لِلنَّبِيِّ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَنْ يَسْتَغْفِرُوا لِلْمُشْرِكِينَ} [التوبة: 113]، وَأَنْزَلَ اللهُ فِي أَبِي طَالِبٍ، فَقَالَ لِرَسُولِ اللهِ صلى الله عليه وسلم: {إِنَّكَ لا تَهْدِي مَنْ أَحْبَبْتَ وَلَكِنَّ اللهَ يَهْدِي مَنْ يَشَاءُ} [القصص: 56].
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4772]
المزيــد ...
ሰዒድ ቢን ሙሰየብ ከአባታቸው እንዳስተላለፉት እንዲህ አሉ፦
"አቡ ጧሊብን ሞት የቀረባቸው ጊዜ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደርሳቸው መጡ። አቡጧሊብ ዘንድም አቡጀህልንና ዐብደላህ ቢን አቢ ኡመያህ ቢን ሙጚራን አገኙ። ለአቡጧሊብም እንዲህ አሉ 'አጎቴ ሆይ! በርሷ ምክንያት አላህ ዘንድ የምሟገትልህን ቃል ላኢላሃ ኢለሏህ በል!' አቡጀህልና ዐብደላህ ቢን አቢ ኡመያህም 'ከዐብዱልሙጦሊብ መንገድ ትሸሻለህን?!' አሉ። አቡጧሊብም የመጨረሻው ንግግሩ 'በዐብዱል ሙጦሊብ መንገድ ላይ ነኝ!' እስኪል ድረስ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአቡጧሊብ ላይ (እንዲሰልም ሀሳብ) ከማቅረብ እነ አቡጀህልም እነዚህን ቃላቶች ከመደጋገም አልተወገዱም። አቡጧሊብ 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ከማለት እምቢተኛ ሆነ። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'በአላህ እምላለሁ! እስካልተከለከልኩ ድረስ ምህረትን እጠይቅልሃለሁ።' አሉ። አላህም {ለነቢዩና ለነዚያ ላመኑት ለአጋሪዎቹ ምህረትን ሊለምኑ የሚገባ አልነበረም።} [አት-ተውባህ: 113] የሚለውን አወረደ። አላህ በአቡ ጧሊብ ዙሪያም ለአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ በማለት አወረደ {አንተ የወደድከውን ሰው ፈፅሞ አታቀናም። ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል።} [አልቀሶስ:56]"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4772]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አጎታቸው አቡጧሊብ ዘንድ ጣእረሞት ላይ ሳለ ገቡና እንዲህ አሉት: አጎቴ ሆይ! በርሷ ምክንያት አላህ ዘንድ የምመሰክርልህን ቃል "ላኢላሃ ኢለሏህ" በል። አቡጀህልና ዐብደላህ ቢን አቢኡመያህም "አቡጧሊብ ሆይ! የአባትህ የዐብዱልሙጦሊብን መንገድ ትተዋለህን?!" አሉ። የጣኦት አምልኮዋቸውን ለማለት ነው። አቡጧሊብ በመጨረሻ ንግግራቸው ላይ "በዐብዱል ሙጦሊብ መንገድ ላይ ነኝ!" እስኪሉ ድረስም ይህን ከመጎትጎት አልተወገዱም። ይህም የሺርክና የጣኦት አምልኮ መንገድ ነው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ጌታዬ እስካልከለኝ ድረስ ምህረትን እለምንልሃለሁ።" አሉ። ይህ የአላህ ንግግርም ወረደ: {ለነቢዩና ለነዚያ ላመኑት ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢሆኑም እንኳ እነሱ (ከሀዲዎቹ) የእሳት ጓዶች መሆናቸው ከተገለፀላቸው በኋላ ምህረትን ሊለምኑ የሚገባ አልነበረም።} [አት-ተውባህ: 113] በአቡ ጧሊብ ዙሪያም ይህ የአላህ ንግግር ወረደ: {አንተ የወደድከውን ሰው ፈፅሞ አታቀናም። ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል። እርሱም ቅኖቹን አዋቂ ነው።} [አልቀሶስ: 56]" አንተ መቃናቱን የወደድከውን ሰው አታቀናም። በአንተ ላይ ያለው ግዴታ ማድረስ ብቻ ነው። አላህ የሻውን ያቀናል።