عَن عُمَرَ بنِ الخَطَّابِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قال: سَمِعْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«لَا تُطْرُونِي كَمَا أَطْرَتِ النَّصَارَى ابْنَ مَرْيَمَ؛ فَإِنَّمَا أَنَا عَبْدُهُ، فَقُولُوا: عَبْدُ اللهِ وَرَسُولُهُ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 3445]
المزيــد ...

ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡
"ክርስቲያኖች የመርየም ልጅን ሲያሞግሱ ወሰን እንዳለፉት እኔን ስታሞግሱ ወሰን አትለፉ። እኔ የአሏህ ባሪያ ብቻ ነኝ። ስለዚህም የአላህ ባሪያና መልክተኛው በሉኝ።'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3445]

ትንታኔ

ክርስቲያኖች ዒሳ ዓለይሂ ሰላምን በተመለከተ ወሰን እንዳለፉት ሁሉ ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ህዝባቸው እሳቸውን በማሞገስ በኩል፣ በአላህ ባህሪያትና ልዩ ድርጊቶቹ እሳቸውን በመግለፅ፣ የሩቅ እውቀትን እንደሚያውቁ በመሞገት፣ ወይም ከአሏህ ጋር እሳቸውን በመማፀንና በመሳሰሉት መልኩ ወሰን እንዳይታለፍባቸው አስጠነቀቁ። ከዚያም ከአሏህ ባርያዎች መካከል አንዱ መሆናቸውን ገልፀው፤ እሳቸውን "የአሏህ ባርያውና መልዕክተኛው" ብለን እንድንገልፃቸው አሳሰቡ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በማላቅ እና በማወደስ ረገድ ሸሪዓ የደነገገውን ገደብ ከማለፍ መጠንቀቅ ይገባል። ይህም ወደ ሽርክ ስለሚያደርስ ነው።
  2. ይህ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ያስጠነቀቁት ነገር በእውነቱ በዚህ ኡማ ተከስቷል። ይህም የተወሰኑት በአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ፣ ከፊሎች የነቢዩ ቤተሰቦች ላይ፣ ሌሎች ደግሞ ወልዮች ላይ ይህ ያስጠነቀቁትን ነገር በመፈፀም ሽርክ ላይ ወድቀዋል።
  3. የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የአሏህ ባሪያው ናቸው እንጂ ከአምላክ መለያዎች መካከል የትኛውም እንደማይገባቸው ለመጠቆም ራሳቸው የአላህ ባሪያ መሆናቸውን ገለፁ።
  4. ረሱል የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአሏህ የተላኩ መልዕክተኛው በመሆናቸው ሊያምኗቸውና ሊከተሏቸው እንደሚገባ ለመጠቆም ራሳቸውን የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውንም ገለፁ።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (67)