عن عبد الله بن مسعود قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«هَلَكَ الْمُتَنَطِّعُون» قالها ثلاثًا.

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2670]
المزيــد ...

ከዐብደሏህ ቢን መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡
'ፅንፈኞች (ወሰን አላፊዎች) ጠፉ!' ሶስት ጊዜ ደጋገሟት።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2670]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ያመጡትን ሸሪዓዊ ወሰን ያለ ምንም መመሪያና እውቀት ወሰን ተላልፈው በንግግራቸውም ይሁን በተግባራቸው በእምነታቸውም ይሁን በአለማዊ ጉዳያቸው ፅንፍ የሚረግጡ ሰዎች ያለባቸውን ውርደትና ኪሳራ ተናገሩ።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በየትኛውም ጉዳይ በተለይም በዒባዳና ፃድቃንን በማላቅ ረገድ ወሰን ማለፍና ያላቅም መንጠራራት መከልከሉንና ከእንዲህ አይነቱ ነገር መራቁ በየትኛውም ጉዳይ ላይ እንደሚበረታታ እንረዳለን።
  2. በአምልኮም ይሁን በሌላው ጉዳይ ተስተካክሎ የተሟላውን መፈለግ እንደሚገባና ይህም የሚሆነው ሸሪዓውን በመከተል መሆኑን እንረዳለን።
  3. አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ጠንከር ማድረግ እንደሚገባ፤ ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህንኑ እንኳ ሲናገሩ ሶስት ጊዜ ደጋግመው ነውና የተናገሩት።
  4. የእስልምና ገራገርነትና ቀላልነትን እንረዳለን።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (67)
ተጨማሪ