عَنْ عَبْدِ اللهِ بنِ مَسْعُودٍ رضي الله عنه قال:
قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم كَلِمَةً وَقُلْتُ أُخْرَى، قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم: «مَنْ مَاتَ وَهُوَ يَدْعُو مِنْ دُونِ اللهِ نِدًّا دَخَلَ النَّارَ» وَقُلْتُ أَنَا: مَنْ مَاتَ وَهُوَ لَا يَدْعُو لِلهِ نِدًّا دَخَلَ الْجَنَّةَ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4497]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዷን ተናገሩ እኔ ደግሞ ሌላዋን ተናገርኩ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: ‹ ከአላህ ውጪ ሌላን ቢጤን (ባላንጣን) እየተጣራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።› እኔ ደግሞ: ‹ለአላህ ሌላን ቢጤን (ባላንጣን) ሳይጣራ የሞተ ሰው ጀነት ይገባል።› አልኩኝ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4497]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአላህ ውጪ ያለን አካል መጣራትና ከአላህ ውጪ ካለ አካል እርዳታ መፈለግን የመሰለ ለአላህ ሊደረግ ግዴታ የሆነን አንዳች ነገር ለሌላ እየሰጠ የሞተ ሰው የእሳት ባለቤት መሆኑን ነገሩን። ኢብኑ መስዑድም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በአላህ አንዳችን ሳያጋራ የሞተ ሰው መመለሻው ወደ ጀነት ነው የሚለውን ጨመሩ።