عن جابر بن عبد الله رضي الله عنهما قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«مَنْ لَقِيَ اللهَ لَا يُشْرِكُ بِهِ شَيْئًا دَخَلَ الْجَنَّةَ، وَمَنْ لَقِيَهُ يُشْرِكُ بِهِ دَخَلَ النَّارَ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 93]
المزيــد ...
ጃቢር ቢን ዐብደሏህ ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡
"በአሏህ ሳያጋራ አሏህን የተገናኘ ጀነት ገብቷል፤ እያጋራበት አሏህን የተገናኘ ደግሞ እሳት ገብቷል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 93]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በአሏህ ላይ አንዳችም ሳያጋራ የሞተ በተወሰነ ወንጀሉ ተቀጥቶም ቢሆን መመለሻው ወደ ጀነት መሆኑን፤ በአሏህ ላይ አንዳችም አጋርቶ የሞተ ደግሞ ጀሀነም መዘውተሪያው መሆኑን ተናገሩ።