عن سهل بن سعد رضي الله عنه عن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«مَنْ يَضْمَنْ لِي مَا بَيْنَ لَحْيَيْهِ وَمَا بَيْنَ رِجْلَيْهِ أَضْمَنْ لَهُ الْجَنَّةَ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6474]
المزيــد ...

ከሰህል ቢን ሰዕድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡
"በሁለት መንገጭላዎቹ መካከል እና በሁለት እግሮቹ መካከል ያሉትን አካላት (ሊጠብቅ) ዋስትና ለገባልኝ እኔም ጀነትን ዋስትና እገባለታለሁ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6474]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም እነርሱን በሚገባ ከጠበቀ ጀነት የሚገባባቸው የሆኑ ሁለት ጉዳዮችን ተናገሩ።
የመጀመርያው፡ የላቀው አሏህን ከሚያስቆጣ ንግግር ምላስን መቆጠብ፤
ሁለተኛው፡ ብልትን ብልግና ከመፈፀም መጠበቅ ነው።
ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ወንጀል የሚፈፀምባቸው እነዚህ ሁለቱ አካላት ስለሆኑ ነው።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ምላስንና ብልትን መጠበቅ ጀነት ለመግባት ሰበብ መሆኑን እንረዳላን።
  2. ምላስና ብልት ተለይተው የተጠቀሱበት ምክንያት የሰው ልጅ በዱንያውም ሆነ በአኺራው ለሚመጣበት መከራ ዋነኛ ምንጮች ሁለቱ በመሆናቸው ነው።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (67)