عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«حُجِبَتِ النَّارُ بِالشَّهَوَاتِ، وَحُجِبَتِ الْجَنَّةُ بِالْمَكَارِهِ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6487]
المزيــد ...
ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው ረሱል የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡
"ጀሀነም ነፍስያ በምትወዳቸው ስሜታዊ ነገሮች ተጋረደች፤ ጀነት ደግሞ ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተጋረደች።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6487]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ጀሀነም ክልክልን በመዳፈርና ግዴታን ባለመወጣት የመሰሉ ነፍስያ በምትፈልጋቸው ነገሮች መሸፈኗን መከበቧን ገለፁ። በመሆኑም የነፍስያውን ፍላጎት በዚህ ረገድ የተከተለ ለጀሀነም ተገባ። ጀነት ደግሞ ትእዛዝ ላይ በመዘውተር፣ ክልከላን በመተውና በዚሁ ላይ ትዕግስት በማድረግ በመሰሉ ነፍስያ በምትጠላቸው ነገሮች መሸፈኗንና መከበቧን አብራሩ። ስለዚህም በዚህ ረገድ በቁርጠኝነት ነፍስያውን የታገለ ለጀነት የተገባ ሆነ።