عَنْ حَكِيمِ بْنِ حِزَامٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ:
سَأَلْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَأَعْطَانِي، ثُمَّ سَأَلْتُهُ فَأَعْطَانِي، ثُمَّ قَالَ لِي: «يَا حَكِيمُ، إِنَّ هَذَا المَالَ خَضِرٌ حُلْوٌ، فَمَنْ أَخَذَهُ بِسَخَاوَةِ نَفْسٍ، بُورِكَ لَهُ فِيهِ، وَمَنْ أَخَذَهُ بِإِشْرَافِ نَفْسٍ لَمْ يُبَارَكْ لَهُ فِيهِ، وَكَانَ كَالَّذِي يَأْكُلُ وَلاَ يَشْبَعُ، وَاليَدُ العُلْيَا خَيْرٌ مِنَ اليَدِ السُّفْلَى»، قَالَ حَكِيمٌ: فَقُلْتُ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، وَالَّذِي بَعَثَكَ بِالحَقِّ لاَ أَرْزَأُ أَحَدًا بَعْدَكَ شَيْئًا حَتَّى أُفَارِقَ الدُّنْيَا، فَكَانَ أَبُو بَكْرٍ يَدْعُو حَكِيمًا لِيُعْطِيَهُ العَطَاءَ، فَيَأْبَى أَنْ يَقْبَلَ مِنْهُ شَيْئًا، ثُمَّ إِنَّ عُمَرَ دَعَاهُ لِيُعْطِيَهُ، فَيَأْبَى أَنْ يَقْبَلَهُ، فَقَالَ: يَا مَعْشَرَ المُسْلِمِينَ، إِنِّي أَعْرِضُ عَلَيْهِ حَقَّهُ الَّذِي قَسَمَ اللَّهُ لَهُ مِنْ هَذَا الفَيْءِ، فَيَأْبَى أَنْ يَأْخُذَهُ. فَلَمْ يَرْزَأْ حَكِيمٌ أَحَدًا مِنَ النَّاسِ بَعْدَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ حَتَّى تُوُفِّيَ رَحِمَهُ اللَّهُ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2750]
المزيــد ...
ከሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህን መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጠየቅኳቸውና ሰጡኝ። ድጋሚ ጠየቅኳቸውና ሰጡኝ። ከዚያም እንዲህ አሉኝ: "ሐኪም ሆይ! ይህ ገንዘብ ለምለምና ጣፋጭ ነው። ይህንን ገንዘብ ነፍሱ እንደተከበረች (ሳይለምን) የወሰደው ሰው ለርሱ ይባረክለታል። ነፍሱን (ለልመና) በማውጣት የወሰደው ሰው ለርሱ አይባረክለትም። እርሱም እየበላ እንደማይጠግብ ሰው ምሳሌ ነው። ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት።" ሐኪምም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በእውነት በላከዎ ጌታ እምላለሁ! ዱንያን እስከምለያይ ድረስ ከዚህ በኋላ ማንንም አልለምንም። አልኩኝ።"» አቡ በክር ሐኪምን ስጦታ ሊሰጠው ይጠራው ነበር። አንዳችም ከርሱ አልቀበልም ብሎ እምቢ አለ። ከዚያም ዑመር ሊሰጠው ጠራው። ከርሱ ከመቀበልም እምቢ አለ። ዑመርም እንዲህ አለ: "እናንተ ሙስሊሞች ሆይ! እኔ ለሐኪም ከምርኮ ገንዘብ አላህ ድርሻው ያደረገለትን ሐቁን አቀረብኩለት። እርሱ ግን እምቢ አለ።" ሐኪም እስኪሞት ድረስ ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከተቀበለ በኋላ የአንድንም ሰው ገንዘብ በመውሰድ አላጎደለም ነበር።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2750]
ሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- ነቢዩን - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - የዱንያ መጣቀሚያ የምትሆንን ጠየቀና ሰጡት። ድጋሚ ጠየቃቸውና ሰጡት። ከዚያም ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉት: "ሐኪም ሆይ! ይህ ገንዘብ የሚጓጓለትና የሚከጀል ነው። ይህንን ገንዘብ ሳይለምን ነፍሱ እጅግ ሳትጓጓና ችክ ሳይል ያገኘው ሰው ለርሱ ይባረክለታል። ነፍሱን ለሰዎች በማቅረብና በመከጀል ያገኘው ሰው ለርሱ አይባረክለትም። እርሱም እየበላ እንደማይጠግብ ሰው ምሳሌ ነው። ከላይ ያለች ሰጪ እጅ ከታች ካለች ከምትለምን እጅ አላህ ዘንድ የተሻለች ናት።" ሐኪምም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በእውነት በላከዎ ጌታ እምላለሁ! ዱንያን እስከምለያይ ድረስ (አሁን ከሰጡኝ) ከርሶ ገንዘብ በኋላ የማንንም ገንዘብ ለምኜ አላጎድልም።" አልኩኝ። የአላህ መልክተኛ ምትክ አቡ በክር - አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና - ሐኪምን ስጦታ ሊሰጠው ይጠራው ነበር። አንዳችም ከርሱ አልቀበልም ብሎ እምቢ አለ። ከዚያም የአማኞች መሪ ዑመርም - አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና - ሊሰጠው ጠራው። ከርሱ ከመቀበልም እምቢ አለ። ዑመርም እንዲህ አለ: "እናንተ ሙስሊሞች ሆይ! እኔ ለሐኪም ከከሃዲያን ጋር ምንም ጦርነትና ጂሃድ ሳይደረግ ከተሰበሰበ ከምርኮ ገንዘብ አላህ ድርሻው ያደረገለትን ሐቁን አቀረብኩለት። እርሱ ግን እምቢ አለ።" ሐኪም እስኪሞት ድረስም ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከተቀበለ በኋላ የአንድንም ሰው ገንዘብ በመውሰድ አላጎደለም ነበር።