عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المؤْمنينَ رَضيَ اللهُ عنها قَالَت:
قُلْتُ لِلنَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: حَسْبُكَ مِنْ صَفِيَّةَ كَذَا وَكَذَا، -قَالَ أَحدُ الرُّوَاةِ: تَعْنِي قَصِيرَةً- فَقَالَ: «لَقَدْ قُلْتِ كَلِمَةً لَوْ مُزِجَتْ بِمَاءِ الْبَحْرِ لَمَزَجَتْهُ» قَالَتْ: وَحَكَيْتُ لَهُ إِنْسَانًا، فَقَالَ: «مَا أُحِبُّ أَنِّي حَكَيْتُ إِنْسَانًا وَأَنَّ لِي كَذَا وَكَذَا».
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وأحمد] - [سنن أبي داود: 4875]
المزيــد ...
ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
«ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለሰፊያ (ነውር’ኮ) እንዲህ እንዲህ ነገሯ ራሱ ይበቃሃል። አልኳቸው። (አንዱ የሐዲሥ ዘጋቢ እንዲህ እንዲህ ነገሯ ይበቃሃል በማለት የፈለገችው እጥረቷን ነው ብለዋል።) እርሳቸውም "ከባህር ውሃ ጋር ብትቀላቀል የባህሩን ውሃ የምታበላሽ የሆነችን ንግግር ተናገርሽ።" አሏት። "እንዲህም አለች "ለርሳቸው የሆነ ሰው የሚያደርገውን አስመስዬ በድርጊት አሳየኃቸው።" እርሳቸውም "ለኔ እንዲህ እንዲህ ቢሰጠኝ እንኳ ሰውን ማስመሰል አያስደስተኝም (አልወድም)።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 4875]
የአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ከሶፊያ‘ኮ (የፈለገችውም የአማኞች እናትን ነው) ከአካላዊ ነውሮቿ እርሷ አጭር መሆኗ ይበቃሃል።" አለቻቸው። እርሳቸውም "ከባህር ውሃ ጋር ብትቀላቀል ውሃውን አሸንፋ የምትለውጠውንና የምታበላሸውን ንግግር ተናገርሽ።" አሏት። እንዲህም አለች "የሆነን ሰው ዝቅ በማድረግ መልኩ የሚሰራውን ስራ አምሳያ አስመስዬ ሰራሁላቸው።" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ነውሩን መናገር ወይም የሚሰራውን ስራ አስመስዬ በመስራቴ ወይም የሚናገረውን አምሳያ በመናገሬ ለዚህ ተግባር ከዱንያ እጅግ በርካታ ነገር ቢሰጠኝ ራሱ ማድረጉ አያስደስተኝም።" አሉ።