عن أبي هريرة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«اجْتَنِبُوا السَّبْعَ الْمُوبِقَاتِ»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ وَمَا هُنَّ؟ قَالَ: «الشِّرْكُ بِاللهِ، وَالسِّحْرُ، وَقَتْلُ النَّفْسِ الَّتِي حَرَّمَ اللهُ إِلَّا بِالْحَقِّ، وَأَكْلُ الرِّبَا، وَأَكْلُ مَالِ الْيَتِيمِ، وَالتَّوَلِّي يَوْمَ الزَّحْفِ، وَقَذْفُ الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ الْغَافِلَاتِ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

አቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፏል፡
"ሰባት አውዳሚዎችን ተጠንቀቁ!" ሶሓቦችም: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ምን ምን ናቸው?" ብለው ጠየቁ፥ ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በአግባቡ ካልሆነ በስተቀር መግደል፣ አራጣ መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ ጦርነት በተፋፋመ እለት ማፈግፈግ፣ ከዝሙት ዝንጉ የሆኑ ጥብቅ ምእመናትን በዝሙት መዝለፍ ናቸው።" አሉ።

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

የአሏህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኡመታቸውን ከሰባት አውዳሚ ወንጀሎች እንዲርቁ አዘዙ። ምን ምን እንደሆኑ በተጠየቁ ጊዜም ተከታዮቹን ዘረዘሩ፡
የመጀመሪያው : በየትኛውም መልኩ ቢሆን ጥራት ለተገባው አላህ ቢጤን በማድረግ፤ ከአምልኮዎች መካከል ማንኛውም የአምልኮ ዘርፍን ከአሏህ ውጭ ላለ አካል በመስጠት አላህ ላይ ማጋራት መሆኑን ገለፁ፤ በሽርክ የጀመሩበት ምክንያትም ከወንጀሎች ሁሉ ትልቁ ወንጀል ስለሆነ ነው።
ሁለተኛ ድግምት፡ - እየቋጠሩ፣ እያነበነቡ፣ መድሀኒትና ጭሳጭስ እያደረጉ የሚሸርቡትን የሚጠቁም ገላጭ ቃል ሲሆን - ድግምቱ የተደረገበትን ሞት ወይም ህመም ላይ በመጣል፣ ወይም በባልና ሚስት መካከል መለያየትን በመፍጠር ተፅእኖ የሚያሳድር ነው። ድርጊቱ ሰይጣናዊ ስራም እንደመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ በሽርክ እና መጥፎ መናፍስት የሚወዱትን ነገር እያደረጉ ወደነርሱ በመቃረብ የሚከናወን ነው።
ሶስተኛ አስተዳደሩ ተግባራዊ በሚያደርገው ሸሪዓዊ ምክንያት ካልሆነ በቀር አሏህ እርም ያደረጋትን ነፍስ መግደል፤
አራተኛ በመብላትም ይሁን በሌላ መልኩ በመጠቃቀም ወለድን መውሰድ፤
አምስተኛ ለአቅመ አዳም ሳይደርስ አባቱ በሞተበት ታዳጊ ገንዘብ ላይ ወሰን ማለፍ፤
ስድስተኛ ከከሀዲያን ጋር ከሚደረገ ፍልሚያ ማፈግፈግ፤
ሰባተኛ ጥብቅ የሆኑ ጨዋ እንስቶችን መዝለፍ፤ እንደዚሁም ጨዋ ወንዶችን መዝለፍ፤

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከባባድ ወንጀሎች በነዚህ ብቻ የተገደበ ሆኖ አይደለም፤ እነዚህ ለብቻ ሊጠቀሱ የቻሉት ከከባድነታቸውና ከአደገኝነትቸው አኳያ ነው።
  2. አንድ ሰው ነፍስን በመግደሉ ወይም ከእስልምና በኋላ በመካዱ ወይም ትዳር ቀመስ ከሆነ በኋላ ዝሙት በመፈፀሙ መግደል የተፈቀደ ሲሆን ይህም ተግባራዊ የሚደረገው በአስተዳደሩ ነው።