ምድቡ:
+ -

عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو رضي الله عنهما قال: قال رَسولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«أَرْبَعٌ مَنْ كُنَّ فِيهِ كَانَ مُنَافِقًا، وَإِنْ كَانَتْ خَصْلَةٌ مِنْهُنَّ فِيهِ كَانَتْ فِيهِ خَصْلَةٌ مِنَ النِّفَاقِ حَتَّى يَدَعَهَا: مَنْ إِذَا حَدَّثَ كَذَبَ، وإِذَا وَعَدَ أَخْلَفَ، وإذَا خَاصَمَ فَجَرَ، وَإِذَا عَاهَدَ غَدَرَ».

[صحيح] - [رواه البخاري ومسلم] - [الأربعون النووية: 48]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"አራት (ባሕርያት) በእርሱ ላይ ያለበት ሰው ሙናፊቅ ሆኗል፤ ከአራቱ ባህሪዎች ውስጥ አንዱ ያለበት ደግሞ እስኪተዋት ድረስ አንድ የሙናፊቅነት ባህሪ ይኖረዋል፦ ሲናገር ይዋሻል፤ ቀጠሮ የያዘ ጊዜ ያፈርሳል፤ ሲከራከር ወሰን ያልፋል፤ ቃልኪዳን ከገባ በኋላ ቃልኪዳኑን ይክዳል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [رواه البخاري ومسلم] - [الأربعون النووية - 48]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአራት ነገሮች አስጠነቀቁ። እነዚህ አራት ነገሮች አንድ ሙስሊም ላይ የተሰባሰቡ ጊዜ በነዚህ ነገሮች ሰበብ ከመናፍቃን ጋር እጅግ በጣም ይመሳሰላል። ይህ ግን እነዚህ አራት ነገሮች እርሱ ላይ በብዛት የሚስተዋሉ ከሆነ ነው እንጂ አልፎ አልፎ የሚስተዋልበት ከሆነ ግን እዚህ ውስጥ አይካተትም። እነሱም:-
የመጀመሪያው: ሲያወራ ሆን ብሎ ይዋሻል፣ በንግግሩም እውነቱን አይናገርም።
ሁለተኛ: አንድ ቃል ኪዳን ከገባ ቃልኪዳኑን አይሞላም። ቃልኪዳን ለገባለት ሰውም ቃሉን ያፈርሳል።
ሶስተኛ: ቀጠሮን የቀጠረ ጊዜ የገባውን ቃል አይሞላም። ቀጠሮውን ያፈርሳል።
አራተኛ: ከአንድ ሰው ጋር የተጨቃጨቀና የተሟገተ ጊዜ ሙግቱ ሀይለኛ ይሆናል። ከእውነትም ይዘነበላል። እውነትን ላለመቀበልም በተንኮል ጥመትና ውሸትን ይናገራል።
ንፍቅና ማለት ውስጡ ካለው ተቃራኒ የሆነን ነገር ግልፅ ማውጣት ነው። የዚህ ሀሳብም በተመሳሳይ እነዚህን ነገሮች በሚተገብር ላይ ይገኛሉ። ንፍቅናውም ባዋራው፣ በቀጠረው፣ ባመነው፣ በተከራከረውና ቃልኪዳን በገባለት ሰው ሐቅ ላይ ነው እንጂ እስልምናን ግልፅ እያደረገ ክህደትን በመደበቅ በእስልምና ላይ መናፍቅ ሆኗል ማለት አይደለም። ከነዚህ ነገሮች መካከል አንድ ጉዳይ ያለበትም እስኪተወው ድረስ በርሱ ላይ የንፍቅና ባህሪ አለበት።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አንዳንድ የሙናፊቅ ምልክቶች መገለጻቸው እርሱ ላይ ከመውደቅ ለማስፈራራትና ለማስጠንቀቅ ነው።
  2. ከሐዲሡ የተፈለገው ቁምነገር እነዚህ ነገሮች የንፍቅና ጉዳዮች እንደሆኑ፣ ባለቤቱ በነዚህ ጉዳዮች ከመናፍቃን ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ፣ የነርሱን ባህሪ የተላበሰ እንደሆነ ማሳወቅ ተፈልጎ ነው እንጂ እስልምናን ግልፅ እያደረገ ክህደትን የሚደብቅ ሙናፊቅ ሆኗል ለማለት ተፈልጎበት አይደለም። እነዚህ ነገሮች ያመዘኑበት፣ በነርሱ የተሳነፈና ያቃለላቸው አብዛኛው ሰው እምነቱም ብልሹ የሆነ ነው በሚልም ተተርጉሟል።
  3. ገዛሊ እንዲህ ብለዋል: «የሃይማኖት መሰረት በሶስት ነገሮች ላይ የታጠረ ነው:- ንግግር፣ ተግባርና ኒያ ናቸው። በውሸታምነት ንግግራቸው ብልሹ እንደሆነ፣ አደራ በመካድ ድርጊታቸው ብልሹ እንደሆነ፣ ቃልን በማፍረስ ኒያቸው ብልሹ እንደሆነ አስገነዘበ። ምክንያቱም ቃልን ማፍረስ የገባውን ቃል ተቃርኖ የመተው ቁርጠኝነት እስከሌለው ድረስ የሚያስነውር ተግባር አይባልም። ቃሉን ለማክበር ቁርጠኛ ሆኖ ከዚያም እንዳያከብር የሚያደርገው ከልካይ ነገር ወይም ቃሉን ለመለወጥ የተሻለ ሀሳብ ቢያጋጥመው ይህ የሙናፊቅ መለዮ አልተገኘበትም ነው የሚባለው።
  4. ንፍቅና ሁለት አይነት ነው: እምነታዊ ንፍቅና: ይህ ሰውዬውን ከኢማን የሚያስወጣው ነው። ይህም እስልምናን ግልፅ አድርጎ ክህደትን መደበቅ ነው። ሌላው ተግባራዊ ንፍቅና: እርሱም ከመናፍቃን ጋር በባህሪያቸው መመሳሰል ነው። ይህም ሰውዬውን ከኢማን አያስወጣም። ነገር ግን ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።
  5. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ዑለማዎች ባጠቃላይ በቀልቡም በምላሱም አምኖ ነገር ግን እነዚህን ነገሮች የሰራ ሰው በክህደት እንደማይፈረጅና በእሳት የሚዘወትር ሙናፊቅ እንደማይሆን ተስማምተዋል።»
  6. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «የተወሰኑ ዑለሞች እንዲህ ብለዋል: እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተፈለጉት መናፍቃን በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘመን የነበሩ በውሸት አምነናል ብለው የተናገሩ፣ በእምነታቸው ታምነው የካዱ፣ በሃይማኖት ጉዳይ እስልምናን ሊረዱ ቃልገብተው ቃላቸውን ያፈረሱ፣ በሙግቶቻቸው ጥመትን ይዘው የተሟገቱ ናቸው።»
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht المجرية التشيكية الموري الولوف Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ