عَنْ عُمَرَ بْنِ الخَطَّابِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَوْ أَنَّكُمْ كُنْتُمْ تَوَكَّلُونَ عَلَى اللهِ حَقَّ تَوَكُّلِهِ لَرَزَقَكُمْ كَمَا يَرْزَقُ الطَّيْرَ تَغْدُو خِمَاصًا وَتَرُوحُ بِطَانًا».
[صحيح] - [رواه الإمام أحمد، والترمذي، والنسائي، وابن ماجه، وابن حبان في صحيحه، والحاكم] - [الأربعون النووية: 49]
المزيــد ...
ከዑመር ቢን ኸጧብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"በአላህ ላይ ትክክለኛውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ወፍን እንደሚለግሰው ለናንተም ሲሳይን ይለግሳቹህ ነበር። (ወፍ) ተርባ ማልዳ ትወጣለች። ሆዷ (በጥጋብ) ሞልቶ ትመለሳለች።"
[ሶሒሕ ነው።] - [رواه الإمام أحمد والترمذي والنسائي وابن ماجه وابن حبان في صحيحه والحاكم] - [الأربعون النووية - 49]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዱንያዊም በዲናዊም ጉዳይ ጥቅምን በማምጣትና ጉዳትን በመከላከል ረገድ በአላህ ላይ እንድንደገፍ እያነሳሱን ነው። ምክንያቱም ከአላህ በስተቀር የሚሰጥም፣ የሚከለክልም ፣ የሚጎዳም፣ የሚጠቅምም የለምና ነው። ጥቅሞችን የሚያመጡና ጉዳቶችን የሚከላከሉ ሰበቦችን በአላህ ላይ ከእውነተኛ መመካት ጋር እንድንፈፅምም አነሳሱ። ይህንን በማንኛውም ወቅት ከፈፀምን አላህ ወፍን በንጋት የተራበች ሆና ወጥታ ከዚያም በምሽት ሆዷ ሞልቶ በመመለስ እንደሚቀልባት እኛንም ይቀልበን ነበር። ይህም የወፏ ድርጊት ያለመሳነፍና መዳከም ሲሳይን ለመፈለግ የሰራችው የሰበብ አይነት ነው።