ምድቡ:
+ -

عَنِ النَّوَّاسِ بْنِ سِمْعَانَ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«البِرُّ: حُسْنُ الخُلُقِ، وَالإِثْمُ مَا حَاكَ فِي صَدْرِكَ، وَكَرِهْتَ أَنْ يَطَّلِعَ عَلَيْهِ النَّاسُ». وَعَنْ وَابِصَةَ بْنِ مَعْبَدٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: أَتَيْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ: «جِئْتَ تَسْأَلُ عَنِ البِرِّ وَالإِثْمِ»، قُلْتُ: نَعَمْ، قَالَ: «اسْتَفْتِ قَلْبَكَ، البِرُّ: مَا اطْمَأَنَّتْ إلَيْهِ النَّفْسُ، وَاطْمَأَنَّ إلَيْهِ القَلْبُ، وَالإِثْمُ: مَا حَاكَ فِي نَفْسِكَ وَتَرَدَّدَ فِي الصَّدْرِ، وَإِنْ أَفْتَاكَ النَّاسُ وَأَفْتَوْكَ».

[صحيح] - [الحديث الأول: رواه مسلم، والحديث الثاني: رواه أحمد والدارمي.] - [الأربعون النووية: 27]
المزيــد ...

ከነዋስ ቢን ሰምዓን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: ነቢዩ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦
«" በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውንም የጠላኸው ነገር ነው።»

-

ትንታኔ

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ስለበጎ ተግባርና ወንጀል ተናገሩ። እንዲህም አሉ: የበጎ ተግባር ትልቁ ነገር ከአላህ ጋር እርሱን በመፍራት፤ ከፍጡራን ጋር ደግሞ የሚያደርሱብንን አዛ (ችግር) በመቻል፣ ቁጣን በመቀነስ፣ ፊትን በመፍታት፣ ንግግርን በማሳመር፣ ዝምድናን በመቀጠል፣ በመታዘዝ፣ በመራራት፣ በጎ በመስራት፣ መልካም ቤተሰብና ባልደረባ በመሆን መልካም ስነምግባርን መላበስ ነው። በጎ ተግባር ማለት ልብና ነፍስ የረጋበትና የሰከነበት ነገር ነው። ወንጀል ማለት ደግሞ ልብህ ለርሱ ሳይከፈት ነፍስህ ውስጥ የተመላለሰ፣ የከነከነህ አሻሚ ነገር ነው። ስትሰራው ወንጀል ይሆን እያልክ ቀልብህ ውስጥ ጥርጣሬ የሚከሰትበትና የምትፈራው፣ ፀያፍ ስለሆነም አርአያ የሚሆኑ፣ ታላላቅና የተሟላ ስብዕና ያላቸው ሰዎች ፊት ጉዳዩ እንዲታወቅብህ የማትፈልገው ጉዳይህ ነው። ይህም ነፍስ በተፈጥሮዋ ሰዎች መልካም ስራዋን እንዲያውቁላት ነው የምትፈልገው። አንዳንድ ስራዋ ይፋ መውጣቱን ከጠላች ግን ያ ስራ ወንጀል ነውና ምንም መልካም የለውም። በነፍስህ ውስጥ ይህ የብዥታ ምልክት እስካለና በነፍስህ ውስጥ እስከተመላለሰ ድረስ ሰዎች ፈትዋ ቢሰጡህ እንኳ የነርሱን ፈትዋ እንዳትወስድ! ምናልባት ፈትዋ ሰጪው ያለእውቀት ፈትዋ ሰጥቶበት ሊሆን ስለሚችል የጉዳዩ ብዥታነት ትክክለኛ እስከሆነ ድረስ ፈትዋው ብዥታውን የማስወገድ አቅም የለውም። ነገር ግን ፈትዋው የተሰጠው በትክክል የሸሪዓ ማስረጃ ላይ ተመስርቶ ከሆነ ፈትዋ ጠያቂው ልቡ ለመልሱ ክፍት ባይሆንም እንኳ የግዴታ ወደ ፈትዋው ሃሳብ መመለስ ግዴታ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht المجرية التشيكية الموري الولوف Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ