عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ بُسْرٍ رَضِيَ اللَّهِ عَنْهُ قَالَ: أَتَى النَّبِيَّ رَجُلٌ، فَقَالَ: يَا رَسُولَ اللَّهِ! إِنَّ شَرَائِعَ الإِسْلَامِ قَدْ كَثُرَتْ عَلَيْنَا، فَبَابٌ نَتَمَسَّكُ بِهِ جَامِعٌ؟ قَالَ:
«لاَ يَزَالُ لِسَانُكَ رَطْبًا مِنْ ذِكْرِ اللَّهِ».
وفي رواية: مِنْ حَدِيثِ مُعَاذِ بْنِ جَبَلٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: آخِرُ مَا فَارَقْتُ عَلَيْهِ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنْ قُلْتُ: أَيُّ الأَعْمَالِ خَيْرٌ وَأَقْرَبُ إِلَى اللَّهِ؟ قَالَ: «أَنْ تَمُوتَ وَلِسَانُكَ رَطْبٌ مِنْ ذِكْرِ اللَّهِ عَزَّ وَجَلَّ».
[صحيح] - [رواه أحمد والترمذي وابن ماجه وابن حبان] - [الأربعون النووية: 50]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ቡስር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የእስልምና ድንጋጌዎች በርግጥም በኛ ላይ በዙብን። አጥብቄ የምይዘውን ዋናውን በር ይንገሩን።" እርሳቸውም እንዲህ አሉ:
"ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [رواه أحمد والترمذي وابن ماجه وابن حبان] - [الأربعون النووية - 50]
አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከደካማነቱ አንፃር ግዴታ ያልሆኑ አምልኮዎች እስኪያቅቱት ድረስ መብዛታቸው እንደተሰማው ስሞታ አቀረበ። ቀጥሎም ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ብዙ ምንዳ የሚያመጣለት የሆነን አጥብቆ የሚይዘውን ቀላል ስራ እንዲጠቁሙት ጠየቀ።
ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሁሉም ሁኔታና ወቅት ምላሱ በ"ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ በ"ተሕሚድ" (አልሐምዱሊላህ)፣ ምህረት በመጠየቅ (አስተጝፊሩሏህ)፣ ዱዓ በማድረግና በመሳሰሉት አላህን በማውሳት ዘውትሮ ምላሱን ማንቀሳቀስና ማርጠብ እንዳለበት ጠቆሙት።