ምድቡ:
+ -

عَنْ أَبِي بُرْدَةَ، عَنْ أَبِيهِ أَبِي مُوسَى الأَشْعَريِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ:
أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بَعَثَهُ إِلَى اليَمَنِ، فَسَأَلَهُ عَنْ أَشْرِبَةٍ تُصْنَعُ بِهَا، فَقَالَ: وَمَا هِيَ؟، قَالَ: «البِتْعُ وَالمِزْرُ»، فَقِيلَ لِأَبِي بُرْدَةَ: مَا البِتْعُ؟ قَالَ: نَبِيذُ العَسَلِ، وَالمِزْرُ: نَبِيذُ الشَّعِيرِ، فَقَالَ: «كُلُّ مُسْكِرٍ حَرَامٌ» خرجه البخاري. وَخَرَّجَهُ مُسْلِمٌ وَلَفْظُهُ: قَالَ: بَعَثَنِي رَسُولُ اَلله أَنَا وَمُعَاذٌ إِلَى اَليَمَنِ، فَقُلْتُ: يَا رَسُولُ اَللَّهِ! إِنَّ شَرَابًا يُصْنَعُ بِأَرْضِنَا يُقَال لَهُ: المِزَرُ مِنَ الشَّعِيرِ، وَشَرَابٌ يُقَالُ لَهُ: البِتْعُ مِنَ العَسَلِ، فَقَالَ: «كُلُّ مُسْكِرٍ حَرَامٌ». وَفِي رِوَايَةٍ لِمُسْلِمٍ: «فَقَالَ: كُلُّ مَا أَسْكَرَ عَنِ الصَّلَاةِ فَهُوَ حَرَامٌ». وَفِي رِوَايَةٍ لَهُ: «وَكَانَ رَسُولُ الله قَدْ أُعْطِيَ جَوَامِعَ الكَلِمِ بِخَوَاتِمِهِ، فَقَالَ: أَنْهَى عَنْ كُلِّ مُسْكِرٍ أَسْكَرَ عَنْ الصَّلَاةِ».

[صحيح] - [رواه البخاري ومسلم] - [الأربعون النووية: 46]
المزيــد ...

ከአቡ ቡርዳህ እንደተላለፈው: እርሳቸው ከአባታቸው አቡ ሙሳ አልአሽዓሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳስተላለፉት አቡ ሙሳ እንዲህ አሉ:
«ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ወደ የመን ላኩት። በየመን ውስጥ ይሰራ ስለነበር መጠጥም ጠየቃቸው። እርሳቸውም "ምንድናት?" አሉት። እርሱም: "ቢትዕ እና ሚዝር ናቸው።" አላቸው። (ሐዲሡን እያስተላለፈ ላለው) ለአቡ ቡርዳ "ቢትዕ ምንድን ነው?" ተብሎ ተጠየቀ። እርሱም "በማር የሚሰራ አስካሪ መጠጥ ነው።" አላቸው። "ሚዝርስ?" ብለው ሲጠይቁት "በገብስ የሚሰራ አስካሪ መጠጥ ነው።" ብሎ መለሰላቸው። ነቢዩም "ሁሉም አስካሪ ነገር ሐራም ነው።" ብለው መለሱለት።»

-

ትንታኔ

አቡ ሙሳ አልአሽዓሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተናገሩት: ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ወደ የመን ላኩት። በየመን መሬት ስለሚሰራ መጠጥ ክልክል ስለመሆኑ ጠየቃቸው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ስለመጠጡ ምንነት ዝርዝር ጉዳይ ጠየቁት። አቡ ሙሳም - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - "ቢትዕ ከማር የሚሰራ አስካሪ መጠጥ ሲሆን ሚዝር ደሞ ከገብስ የሚሰራ አስካሪ መጠጥ ነው።" ብለው ተናገሩ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ንግግርን ሰብስቦ የመናገር ተሰጥዖ ተሰጥቷቸዋልና "ሁሉም አስካሪ ሐራም ነው።" አሉት።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዝ ማለት: ተምር ወይም ማር ወይም ገብስና የመሳሰሉት ውሃ ውስጥ ይጨመሩና በርሱ ጣፋጭ ጣዕም ያለው መጠጥ ይሰራበታል። ከዚህ በኋላ ወደ አስካሪነት መጠጥነት ይለወጣል። ያሰክራልም።
  2. ይህ ሐዲሥ ሁሉንም አስካሪ አይነቶችን እንደአስካሪ መጠጥ፣ ሐሺሽና የመሳሰሉትን ክልክል ለማድረግ መርህ የሆነ ሐዲሥ ነው።
  3. አንድ ሙስሊም የሚያስፈልገውን ነገር መጠየቁ ወሳኝ ነገር እንደሆነ እንረዳለን።
  4. አስካሪ መጠጥ መጀመሪያ ክልክል የተደረገው የሶላት ወቅት በሚደርስ ጊዜ ብቻ ነበር። አንድ ሙሃጂር ሲሰግድ ሶላቱ ውስጥ ሲቀራ በአቀራሩ ላይ ሲቀላቅል ግን ይህ የአላህ ንግግር ወረደ: {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እናንተ የሰከራችሁ ሆናችሁ የምትሉትን ነገር እስከምታውቁ ድረስ ስግደትን አትቅረቡ።} [አንኒሳእ: 43] የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለፋፊ "ሰካራም ሶላት ዘንድ እንዳይቀርብ!" በማለት ይለፍፍ ነበር። ቀጥሎ አላህ እንዲህ በማለት ባጠቃላይ ከለከለው: {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ፣ ቁማርም፣ ጣዖታትም፣ አዝላምም ከሰይጣን ስራ የሆኑ እርኩስ ብቻ ናቸው። (እርኩስን) ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና። [90] ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል አላህን ከማውሳትና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው። ታዲያ እናንተ (ከእነዚህ) ተከልካዮች ናችሁን (ተከልከሉ።)} [አልማኢዳህ: 90 -91]
  5. አላህ አስካሪ መጠጥን የከለከለው ከባባድ ጉዳቶችንና ብልሽቶችን ያካተተ ስለሆነ ነው።
  6. ለክልከላው ታሳቢ የሚደረገው ወሳኙ ጉዳይ የአስካሪነት ባህሪው መገኘቱ ነው። ብርዙ የአስካሪነትን ባህሪ ከተላበሰ ክልክል ነው። የአስካሪነትን ባህሪ ካልተላበሰ ደግሞ ይፈቀዳል።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht المجرية التشيكية الموري الولوف Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ