عَنْ أَبِي مُحَمَّدٍ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرِو بْنِ العَاصِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَا يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ حَتَّى يَكُونَ هَوَاهُ تَبَعًا لِمَا جِئْتُ بِهِ».
[قال النووي: حديث صحيح] - [رويناه في كتاب الحجة بإسناد صحيح] - [الأربعون النووية: 41]
المزيــد ...
ከአቡ ሙሐመድ ዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዓስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦
"አንዳችሁ ዝንባሌው ይዤ የመጣሁትን እስከሚከተል ድረስ አላመነም።"
-
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አንድ ሰው ውዴታው መልክተኛው -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይዘውት የመጡትን ትእዛዛትን፣ ክልከላዎችንና ሌሎችንም እስከሚከተል ድረስ፤ እርሳቸው ያዘዙትን እስኪወድና የከለከሉትንም እስኪጠላ ድረስ ኢማኑ የተሟላ አማኝ አይሆንም ብለው አብራሩ።