ምድቡ:
+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَة رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُول اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إنَّ اللَّهَ تَعَالَى قَالَ: مَنْ عَادَى لِي وَلِيًّا فَقْد آذَنْتُهُ بِالحَرْبِ، وَمَا تَقَرَّبَ إلَيَّ عَبْدِي بِشَيْءٍ أَحَبَّ إلَيَّ مِمَّا افْتَرَضْتُ عَلَيْهِ، وما يَزَالُ عَبْدِي يَتَقَرَّبُ إلَيَّ بِالنَّوَافِلِ حَتَّى أُحِبَّهُ، فَإِذَا أَحْبَبْتُهُ كُنْتُ سَمْعَهُ الَّذِي يَسْمَعُ بِهِ، وَبَصَرَهُ الَّذِي يُبْصِرُ بِهِ، وَيَدَهُ الَّتِي يَبْطِشُ بِهَا، وَرِجْلَهُ الَّتِي يَمْشِي بِهَا، وَإِنْ سَأَلَنِي لَأُعْطِيَنَّهُ، وَلَئِنْ اسْتَعَاذَنِي لَأُعِيذَنَّهُ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [الأربعون النووية: 38]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ እንዲህ ብሏል: ‹የኔን ወዳጅ (ወሊይ) ጠላት አድርጎ የያዘን ሰው በርግጥም ጦርነት እንዳወጀኩበት አሳውቄዋለሁ። ባሪያዬ ግዴታ ካደረግኩበት በበለጠ ወደ እኔ ተወዳጅ በሆነ በአንዳችም ነገር አይቃረብም። ባሪያዬ ወደ እኔ በትርፍ ስራዎች ከመቃረብ አይወገድም የምወደው ቢሆን እንጂ፤ የወደድኩትም ጊዜ የሚሰማበት መስሚያው እሆነዋለሁ፣ የሚያይበት መመልከቻ እሆነዋለሁ፣ የሚጨብጥበት እጅ እሆነዋለሁ፣ የሚራመድበት እግር እሆነዋለሁ፣ ቢጠይቀኝ እሰጠዋለሁ፣ ከኔ ጥበቃ ከፈለገም እጠብቀዋለሁ።›"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [الأربعون النووية - 38]

ትንታኔ

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሐዲሠል ቁድስ አላህ እንዲህ እንዳለ ተናገሩ: ከወዳጆቼ መካከል አንድንም የኔን ወዳጅ ያወከና ያስቆጣ ከኔ ጋር ጠላት እንደሆነ አውጄያለሁም አሳውቄዋለሁም። ወሊይ ማለት: አላህን ፈሪ አማኝ ነው። አንድ ባሪያ ባለው ኢማንና ፈሪሃ አላህነት ልክ የአላህ ወሊይነት ይኖረዋል። አንድ ሙስሊም አላህ ግዴታ ያደረገበትን ትእዛዛትን መፈፀምና ክልክሎችን መተውን ያህል ወደ አላህ የሚያቃርበው ጌታው ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ምንም ነገር የለም። አንድ ሙስሊም ወደ ጌታው ከግዴታዎች በተጓዳኝ በትርፍ ስራዎች ከመቃረብ አይወገድም የአላህን ውዴታ የሚያገኝ ቢሆን እንጂ፤ አላህ የወደደው ጊዜም አላህ እነዚህን አራት አካላቶቹን ያቀናለታል: በመስሚያው ያግዘዋል። አላህን ከሚያስደስት ነገር ውጪ ሌላ ምንም አይሰማም። በመመልከቻው ያግዘዋል። አሏህ እንዲታይ የሚወደውንና የሚያስደስተውን ነገር እንጂ ሌላ አይመለከትም። እጁንም ያግዘዋል። በእጁ አላህን ከሚያስደስት ነገር በቀር አይሰራም። አላህን ወደሚያስደስት ነገር ካልሆነ በቀር እንዳይራመድ በማድረግም እግሩንም ያግዘዋል። መልካም ነገር ወዳለበት ካልሆነ በቀርም አይንቀሳቀስም። ከዚህም ጋር አላህን አንዳች ነገር ከጠየቀው አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፤ ተማፅኖውንም የሚሰማው ይሆናል። የአላህ ጥበቃ ካስፈለገውና የአሏህን ከለላ ፈልጎ ከተጠጋ ጥራት የተገባው አላህም ከሚፈራው ነገር ይጠብቀዋል።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ይህ ሐዲሥ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጌታቸው ከሚዘግቡት ሐዲሥ አንዱ ነው። "ሐዲሠል ቁድስ" ወይም "ሓዲሠል ኢላሂይ" በመባል ይጠራል። እርሱም ቃሉም ሆነ መልዕክቱ ከአላህ የሆነ ሲሆን ነገር ግን ቁርአን ከሌላው የተለየበት የሆኑ መለዮዎች የሉትም። ለምሳሌ: ሲያነብ በየፊደላቱ አጅር ማስገኘቱ፣ እርሱን ለማንበብ ዉዱእ ማድረግ፣ ከቻሉ አምሳያውን እንዲያመጡ የተሞገተበት መሆን፣ የቃል አወቃቀሩ መለኮታዊነትና ከዚህም ውጪ ያሉ የቁርአን መለዮዎች የሉትም ማለት ነው።
  2. የአላህን ወዳጆች ከማወክ መከልከሉ፤ እነርሱን በመውደድና ደረጃቸውን በማወቅ ላይም መነሳሳቱን እንረዳለን።
  3. የአላህን ጠላቶችን በመጣላት ላይ መታዘዙንና እነርሱን መወዳጀት መከልከሉን እንረዳለን።
  4. የአላህን ሸሪዓ ሳይከተል የአላህን ወዳጅነት የሞገተ ሰው በሙግቱ ውሸታም መሆኑን እንረዳለን።
  5. የአላህ ወዳጅነት ግዴታዎችን በመፈፀምና ክልክሎችን በመተው ነው የሚገኘው።
  6. ለአንድ ባሪያ የአላህን ውዴታና የዱዓን ተቀባይነት ከሚያስገኙለት ምክንያቶች መካከል ግዴታዎችን ከፈፀመና ክልክሎችን ከተወ በኋላ ትርፍ ስራዎችን መስራት ነው።
  7. የወሊዮች ልቅናና የደረጃቸው ከፍታ መጠቆሙን እንረዳለን።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الليتوانية الدرية الصربية الطاجيكية Kinjaruandisht المجرية التشيكية الموري ጣልያንኛ Kannadisht الولوف Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية الخميرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ምድቦች
ተጨማሪ