عَنْ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِيمَا يَرْوِي عَنْ رَبِّهِ تَبَارَكَ وَتَعَالَى، قَالَ:
«إنَّ اللهَ كَتَبَ الحَسَنَاتِ وَالسَّيِّئَاتِ، ثُمَّ بَيَّنَ ذَلِكَ، فَمَنْ هَمَّ بِحَسَنَةٍ فَلَمْ يَعْمَلْهَا؛ كَتَبَهَا اللهُ عِنْدَهُ حَسَنَةً كَامِلَةً، وَإِنْ هَمَّ بِهَا فَعَمِلَهَا؛ كَتَبَهَا اللهُ عِنْدَهُ عَشْرَ حَسَنَاتٍ إلَى سَبْعِمِائَةِ ضِعْفٍ إلَى أَضْعَافٍ كَثِيرَةٍ، وَإِنْ هَمَّ بِسَيِّئَةٍ فَلَمْ يَعْمَلْهَا؛ كَتَبَهَا اللهُ عِنْدَهُ حَسَنَةً كَامِلَةً، وَإِنْ هَمَّ بِهَا فَعَمِلَهَا؛ كَتَبَهَا اللهُ سَيِّئَةً وَاحِدَةً».
[صحيح] - [رواه البخاري ومسلم في صحيحيهما بهذه الحروف] - [الأربعون النووية: 37]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከተከበረውና ከላቀው ጌታቸው በሚያስተላልፉት (ሐዲሠል ቁድሲይ) እንዲህ አሉ፦
"አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል። ይህንንም አብራርቶታል። አንድን መልካም ስራ (ለመስራት) አስቦ ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳን ይጽፍለታል። እሱ (ለመስራት) አስቦ ከሰራት ደግሞ አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ (ከዛም በላይ) እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ የሚደርስ ምንዳዎችን ይጽፍለታል። አንድን ኃጢዐት (ለመስራት) አስቦ ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳ ይጽፍለታል። እሱ (ለመስራት) ካሰባትና ከሰራት አላህ ለሱ አንዲት ኃጢዐት ይጽፍበታል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [رواه البخاري ومسلم في صحيحيهما بهذه الحروف] - [الأربعون النووية - 37]
መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን እንደወሰነ ከዚያም ለሚፅፉት ሁለት መላእክቶች እንዴት እንደሚፅፉት እንዳብራራ ገለፁ።
መልካምን ለመስራት የፈለገ፣ ያሰበና የቆረጠ ሰው ባይሰራትም እንኳ ለሱ አንድ ምንዳ ትፃፍለታለች። ከሰራት ደግሞ በስራዋ አምሳያ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ከዚያም አልፎ እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ ትባዛለች። ይህ የምንዳ ጭማሪው ቀልቡ ውስጥ ባለው ኢኽላስ፣ በጥቅሙ ወደ ሌሎች ተሻጋሪነትና በመሳሰሉት ልክ ተንተርሶ ነው ።
ኃጢዐትን ለመስራት የፈለገ፣ ያሰበና የቆረጠ ከዚያም ለአላህ ብሎ ሳይሰራት የተዋት ሰው ለሱ አንድ ምንዳ ይጻፍለታል። ወደዛች ኃጢዐት የሚያዳርሱ መንስኤዎችን ካለመፈፀም ጋር በሌላ ነገር በመጠመዱ ሳቢያ ከተዋት ምንም ነገር አይፃፍለትም። ኃጢዐቱን መስራት ስለተሳነው ከተወ ደግሞ በሱ ላይ ያለመው ትፃፍበታለች። ከሰራት ደግሞ አንዲት ሀጢዐት ትፃፍበታለች።