عَن ابنِ عباسٍ رضي الله عنهما أنَّ رسولَ اللهِ صلي الله عليه وسلم قال:
«لَو يُعطَى النّاسُ بدَعواهُم لادَّعَى رِجالٌ أموالَ قَومٍ ودِماءَهُم، لَكِنَّ البَيِّنَةَ على المُدَّعِى، واليَمينَ على مَن أنكَرَ».
[حسن] - [رواه البيهقي، وغيره هكذا، وبعضه في الصحيحين] - [الأربعون النووية: 33]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ሰዎች በሙግታቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም (ለመውሰድ) ይሞግቱ ነበር። ነገር ግን ማስረጃ በከሳሽ ላይ፣ መሀላ ደግሞ ክሱን ባወገዘ ሰው ላይ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ተደረገ።"
[ሐሰን ነው።] - [رواه البيهقي وغيره هكذا وبعضه في الصحيحين] - [الأربعون النووية - 33]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰዎች ያለማስረጃና ያለ ጠቋሚ ማስረጃ በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም ለመውሰድ ይከሱ እንደነበር፤ ነገር ግን ከሳሽ ለፈለገው ጉዳይ ማስረጃ የማስቀደም ግዴታ እንዳለበት ማስረጃ ከሌለው ደግሞ ክሱ ወደ ተከሳሽ ይቀርብና ክሱን ካወገዘው በመማል ራሱን ከጥፋተኝነት እንደሚያነፃ ገለፁ።