عَنْ أَبِي سَعِيدٍ سَعْدِ بْنِ مَالِكِ بْنِ سِنَانٍ الخُدْرِيّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَا ضَرَرَ وَلَا ضِرَارَ».
[حسن] - [رواه ابن ماجه، والدارقطني، وغيرهما مسندًا] - [الأربعون النووية: 32]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ ሰዕድ ቢን ማሊክ ቢን ሲናን አልኹድሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ራስን መጉዳትም ሆነ ሌላውን መጉዳት የለም።"
-
ነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጉዳትን በማንኛውም አይነት መገለጫው ከነፍስ ላይም ይሁን ከሌሎች ላይ መከላከል ግዴታ እንደሆነ ገለፁ። ስለሆነም አንድ ሰው ራሱንም ይሁን በተመሳሳይ መልኩ ሌላንም ቢሆን ማወክ አይፈቀድለትም። እንዲሁም ጉዳትን በጉዳት መመለስም አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ወሰን ባልታለፈበት የማመሳሰል (የቂሷስ ህግ) ካልሆነ በስተቀር ጉዳት በመጉዳት አይወገድምና።