عن عائشة أم المؤمنين وعبد الله بن عباس رضي الله عنهما قالا:
لَمَّا نَزَلَ بِرَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ طَفِقَ يَطْرَحُ خَمِيصَةً لَهُ عَلَى وَجْهِهِ، فَإِذَا اغْتَمَّ بِهَا كَشَفَهَا عَنْ وَجْهِهِ، فَقَالَ وَهُوَ كَذَلِكَ: «لَعْنَةُ اللَّهِ عَلَى اليَهُودِ وَالنَّصَارَى، اتَّخَذُوا قُبُورَ أَنْبِيَائِهِمْ مَسَاجِدَ» يُحَذِّرُ مَا صَنَعُوا.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 435]
المزيــد ...
ከእናትችን ዓኢሻና ዐብደላህ ቢን ዓባስ - (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
"የሞት መልዐክ በአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ የወረደ ጊዜ ፊታቸው ላይ ጨርቃቸውን ጣል ማድረግ ጀመሩ ፤ ሲያፍናቸው ደግሞ ይገልጧት ነበር ፤ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ 'በአይሁድ እና ክርስቲያኖች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ ! የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው ያዙ።' አሉ፤ ከሰሩት ስራ እያስጠነቀቁ። '"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 435]
እናታችን ዓኢሻና ኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሞት የቀረባቸው ጊዜ የጨርቅ ቁራጭ ፊታቸው ላይ ጣል ያደርጉ እንደነበርና በሞት ስካር ሳቢያ ለመተንፈስ ያስቸገራቸው ጊዜም ከፊታቸው ያስወግዱት እንደነበር ነገረችን። በዚህ ከባድ ሁኔታ ላይ እያሉ አላህ አይሁድና ክርስቲያኖችን እንደረገመ፤ ከእዝነቱም እንዳራቀ፤ ይህም በነቢያቶቻቸው መቃብር ላይ መስገጃ በመገንባታቸው ምክንያት መሆኑን ነገረችን። የጉዳዩ አደገኛነት ከባድ ባልነበር በእንደዚ አይነት ሁኔታ ላይ ሆነው አይጠቅሱትም ነበር። ስለዚህም ይህ የአይሁዶችና ክርስቲያኖች ድርጊት እንዲሁም በአላህ ላይ ወደ ማጋራት የሚያዳርስ ነውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ መሰል ድርጊቶች ላይ ከነርሱ ጋር መመሳሰልን ከለከሉ።