عن أبي هريرة رضي الله عنه قال:
كان رسولُ الله صلى الله عليه وسلم إذا عَطَس وضَعَ يَدَه -أو ثوبَهُ- على فيهِ، وخَفَضَ -أو غضَّ- بها صوتَهُ.
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وأحمد] - [سنن أبي داود: 5029]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ድምፃቸውን ይቀንሱበት ነበር።»
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 5029]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ:
መጀመሪያ: ከአፋቸው ወይም ከአፍንጫቸው አንዳች ነገር ወጥቶ አብሯቸው የተቀመጠውን ላለማወክ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ ያኖራሉ።
ሁለተኛ: ድምፃቸውን ይቀንሱ ነበር። ከፍም አያደርጉትም።