የሓዲሦች ዝርዝር

አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድ ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ላይ አምስት መብቶች አሉት፤ ሰላምታ መመለስ፣ ህመምተኛ መጠየቅ፣ ጀናዛን መሸኘት፣ ጥሪውን መቀበልና ባስነጠሰው ጊዜ 'የርሐሙከሏህ' ማለት ናቸው።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሲገናኙ ይህም እየዞረ ያኛውም እየዞረ ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ከሁለቱ ምርጡ በሰላምታ የሚጀምረው ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሽቶን አይመልሱም ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
'አላህ ባሪያው ምግብን በልቶ እንዲያመሰግነው ወይም መጠጥን ጠጥቶ እንዲያመሰግነው ይወዳል።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንተ ልጅ ሆይ! ቢስሚላህ በል! በቀኝህ ብላ፣ ፊትህ ካለውም ብላ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ የበላ ጊዜ በቀኙ ይብላ። የጠጣም ጊዜ በቀኙ ይጠጣ። ሰይጣን የሚበላውም በግራው፤ የሚጠጣውም በግራው ነውና።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የቀጭን ሐርንና የወፍራም ሐርን ልብስ አትልበሱ! በወርቅና ብር እቃ አትጠጡ! በ(ወርቅና ብር) ትሪም አትብሉ! እርሷ በዚህ ዓለም ለነርሱ ናት፤ በመጪው ዓለም ደግሞ ለኛ ናት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
በዱንያ ሐር የለበሰ ሰው በመጪው ዓለም አይለብሰውም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ እየሸና ሳለ ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዘው፤ ሲፀዳዳም በቀኝ እጁ አይጥረግ፤ በእቃ ውስጥም አይተንፍስ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ የሚወደውን ህልም በተመለከተ ጊዜ እርሷ ከአላህ ናትና በርሷ ምክንያት አላህን ያመስግንም ለሌሎችም ያውራት፤ ከዚህ ውጪ የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ጊዜ ደሞ እርሷ ከሸይጧን ናትና ከክፋቷ በአላህ ይጠበቅ፤ ለአንድም ሰው አያውራ። እርሷም አትጎዳውም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ድምፃቸውን ይቀንሱበት ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድ ሰውዬ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በግራ እጁ በላ። እርሳቸውም 'በቀኝህ ብላ።' አሉት። እርሱም 'አልችልም!' አላቸው። እርሳቸውም 'አያስችልህ!' አሉት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ ወንድሙን ያገኘ ጊዜ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ! በመካከላቸው ዛፍ ወይም ግድግዳ ወይም ድንጋይ ከጋረዳቸው ከዚያም ድጋሚ ቢያገኘው በድጋሚ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
መልካም ህልም ከአላህ ነው። መጥፎ ህልም ከሸይጧን ነው። አንዳችሁ የሚፈራውን መጥፎ ህልም የተመለከተ ጊዜ ወደ ግራው ይትፋ፤ ከህልሙ ክፋትም በአላህ ይጠበቅ። ያኔ እርሷም አትጎዳውም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የአላህ መልክተኛ ሆይ! መዳኛ ምንድን ነው? አልኳቸው። እርሳቸውም "ምላስህን ተቆጣጠር፤ ቤትህ ይስፋህ፤ በወንጀልህም ላይ አልቅስ!" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ብሰራው ጀነት የምገባበትን ስራ ጠቁሙኝ!' እርሳቸውም እንዲህ አሉት 'በርሱ ላይ አንዳችም ሳታጋራበት አሏህን ማምለክ፣ ግዴታ ሶላትን መስገድ፣ ግዴታ የሆነውን ዘካ መስጠት፣ ረመዷንን መጾም ነው።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የሚጋልብ ሰው በእግረኛ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ በተቀማጭ ላይ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን በሰላምታ አትጀምሯቸው። ከመካከላቸው አንዱን መንገድ ላይ ባገኛችሁ ጊዜም ወደ ጠባቡ መንገድ አጣብቡት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደኛ መጡ። እኛም እንዲህ ብለን ጠየቅናቸው የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶ ላይ እንዴት ሰላምታ እንደምናቀርብ አውቀናል። በርሶ ላይ ሶላት የምናወርደውስ እንዴት ነው?
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የማለ ሰው በመሀላውም 'በላትና ዑዛ እምላለሁ' ያለ ሰው 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ይበል። ለባልደረባው 'ና ቁማር እንጫወት' ያለ ሰውም ይመፅውት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከት! ሴት ልጅም ወደ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ አትመልከት!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው፤ ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ቁርኣንን ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነብ ምፅዋትን በይፋ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው፤ ቁርኣንን በዝግታ የሚያነብ ምፅዋትን በድብቅ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አራት ነገሮች ያሉበት ሰው ጥርት ያለ ሙናፊቅ ይሆናል። ከነርሱ መካከል ከፊሉ ያለበት ሰው እስኪተወው ድረስ ከፊል ንፍቅና ይኖርበታል። ሲያወራ ይዋሻል፣ ቃልኪዳን ይዞ ያፈርሳል፣ ቀጠሮ ይዞ ያፈርሳል፣ ሲሟገት (ድንበር ያልፋል) በጥመት ላይ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሙእሚን የሆነ ሰው እጅግ ተቺ፣ እጅግ ተራጋሚ፣ ፀያፍ ተግባር ሰሪ፣ መጥፎ ንግግር ተናጋሪ አይደለም።
عربي እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ
አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመምጣት "አስሰላሙ ዐለይኩም" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። ቀጥሎም ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "አስር" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድ ሙስሊም ሴት የአንድ ምሽት መንገድ ከርሷ ጋር የዝምድና ባለቤት የሆነ ወንድ ከሌለ በቀር ልትጓዝ አልተፈቀደላትም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
የሙስሊም ሽርጥ እስከ ባቱ ግማሽ ድረስ ነው። ከባቱ ግማሽና በቁርጭምጭሚቱ መሃል ቢሆንም ግን ችግር የለውም። ከቁርጭምጭሚት ዝቅ ያለ ከሆነ እርሱ እሳት ውስጥ ነው። ሽርጡን በኩራት የጎተተን ሰው አላህ ወደርሱ አይመለከትም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችሁ ያዛጋ ጊዜ ሸይጧን ወደ ውስጡ ስለሚገባ በእጁ አፉን ይያዝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንድ ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ ያሉት መብቶች ስድስት ናቸው።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምንድን ናቸው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ያገኘኸው ጊዜ ሰላምታን አቅርብለት፤ የጠራህ ጊዜ ጥሪውን አክብር፤ ካንተ ምክርን በፈለገ ጊዜ ምከረው፤ አስነጥሶ አላህን ያመሰገነ ጊዜ "የርሐሙከሏህ" በለው፤ የታመመ ጊዜ ጠይቀው፤ የሞተም ጊዜ ቅበረው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ለኩራት ልብሱን የጎተተን ሰው አላህ አይመለከተውም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አዝሂቢልባስ ረበንናስ ወሽፊ አንተ ሻፊ፤ ላ ሺፋአ ኢላ ሺፋኡክ፣ ሺፋአን ላዩጋዲሩ ሰቀማ"» ትርጉሙም "የሰዎች ጌታ የሆንከው ሆይ! በሽታውን አስወግድ። አንተ ፈዋሽ ነህና ፈውሰው። በሽታን የማያስቀር ከሆነው ከአንተ ፈውስ በቀርም ሌላ ፈውስ የለም።" ማለት ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
መሃላ ሸቀጥን ተፈላጊ የሚያደርግ (የሚያዋድድ)፤ ትርፍን (በረከት) ደግሞ የሚያጠፋ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
አንዳችን ነገር ከኛ ሰምቶ እንደሰማው አድርጎ ያደረሰ ሰው አላህ ያብራው። ከሰማው ሰው የበለጠ (የሰማውን አብልጦ) የሚጠብቅ ስንትና ስንት ሰው አለ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
ማንኛውም ለወንድሙ ‹አንተ ከሀዲ› ያለ ሰው በርግጥም በርሷ (በከሀዲነቷ) ላይ አንዳቸው ወድቀዋል። እንዳለው ሆኖ ከሆነ (መልካም) ያለበለዚያ ወደርሱ ትመለሳለች።
عربي እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ
አላህ ዐዘ ወጀል እንዲህ አለ: ‹የአደም ልጅ ዘመንን በመሳደብ ያውከኛል። ዘመን እኔው ነኝ ፤ ነገሮች በኔ እጅ ናቸው፤ ምሽቱንና ቀኑን የምገለባብጠው እኔ ነኝ።›
عربي ኢንዶኔዥያኛ ቬትናማዊ