عَنْ وَحْشِيِّ بْنِ حَرْبٍ رَضيَ اللهُ عنه:
أَنَّهُمْ قَالُوا: يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنَّا نَأْكُلُ وَلَا نَشْبَعُ، قَالَ: «فَلَعَلَّكُمْ تَأْكُلُونَ مُتَفَرِّقِينَ؟» قَالُوا: نَعَمْ. قَالَ: «فَاجْتَمِعُوا عَلَى طَعَامِكُمْ، وَاذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَيْهِ، يُبَارَكْ لَكُمْ فِيهِ».
[حسن] - [رواه أبو داود وابن ماجه وأحمد] - [سنن ابن ماجه: 3764]
المزيــد ...
ከወሕሺይ ቢን ሐርብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው:
«እነርሱ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ እየበላን አንጠግብም።" አሏቸው። እርሳቸውም "ምናልባት ተበታትናችሁ ለየብቻ እየበላችሁ ይሆን?" ብለው ጠየቋቸው። እነርሱም "አዎን" አሉ። እርሳቸውም "ምግብ ስትበሉ ተሰብሰቡ። (አንድ ላይ ብሉ) የአላህንም ስም በምግባቹ ላይ አውሱ። አላህ ምግባችሁን ይባርክላችኋል።"»
[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ኢብኑ ማጀህ - 3764]
የተወሰኑ ሶሓቦች ነቢዩን - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ በማለት ጠየቁ: "እኛ እንበላለን። ነገር ግን አንጠግብም።"
ነቢዩም - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለነርሱ እንዲህ አሏቸው: "ምን አልባት ስትበሉ ተበታትናችሁ ለየብቻ ነው እንዴ የምትበሉት?" እነርሱም: "አዎን" አሉ። እርሳቸውም: "ተሰብሰቡ ሳትበታተኑ ብሉ። ስትበሉ ቢስሚላህ በማለት የአላህን ስም አውሱ። በዛም ይባረክላችኋልም ትጠግባላችሁም።" አሏቸው።