عَنِ ابْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«أُمِرْتُ أَنْ أُقَاتِلَ النَّاسَ حَتَّى يَشْهَدُوا أَنْ لاَ إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ، وَيُقِيمُوا الصَّلاَةَ، وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ، فَإِذَا فَعَلُوا ذَلِكَ عَصَمُوا مِنِّي دِمَاءَهُمْ وَأَمْوَالَهُمْ إِلَّا بِحَقِّ الإِسْلاَمِ، وَحِسَابُهُمْ عَلَى اللَّهِ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ናቸው ብለው እስኪመሰክሩ፣ ሶላትን ቀጥ አድርገው እስኪሰግዱና ዘካን እስኪሰጡ ድረስ ሰዎችን እንድጋደል ታዝዣለሁ። ይህንን ከፈፀሙ በኢስላም ሐቅ ካልሆነ በቀር ደማቸውና ገንዘባቸውን ከኔ ጠብቀዋል። ሒሳባቸውም አላህ ዘንድ ነው።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim with all its versions]

ትንታኔ

አጋርያን ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ ብቸኛና አጋር እንደሌለው እስኪመሰክሩ፤ በሙሐመድም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መልክተኝነት እስኪመሰክሩና ይህ የምስክር ቃል በሚያስፈርደው ነገሮች እስከሚተገብሩ ለምሳሌ በቀንና ምሽት ውስጥ አምስት ሶላቶችን መስገድ ላይ መጠባበቅ፣ ግዴታ የሆነውን ዘካ ለሚገባው እስኪሰጡ ድረስ አላህ አጋርያንን እንዲጋደሉ እንዳዘዛቸው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተናገሩ። እነዚህን ጉዳዮች የሰሩ ጊዜ ኢስላም ደማቸውንና ገንዘባቸውን ይጠብቅላቸዋል። በኢስላም ህግጋት መሰረት ለግድያ የሚያበቃቸውን ወንጀል ወይም ጉዳት እስካልፈፀሙ ድረስም እነርሱን መግደል አይፈቀድም። ከዚያም እነርሱን መተሳሰቡን የትንሳኤ ቀን ውስጣቸውን በሚያውቀው አላህ ቁጥጥር ይሆናል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ህግጋቶች ተፈፃሚነታቸው በውጫዊ ማንነት መሰረት ነው። ውስጣዊ ማንነትን የሚቆጣጠረው አሏህ ነው።
  2. ወደ ተውሒድ የመጣራት አንገብጋቢነትን እንረዳለን። ዳዕዋ በቅድሚያ የሚጀመረው በተውሒድ ነው።
  3. ይህ ሐዲሥ አጋርያንን ወደ ኢስላም እንዲገቡ ማስገደድ ይገባል ማለት አይደለም። ይልቁንም ወደ ኢስላም በመግባት ወይም ግብር በመክፈል መካከል የመምረጥ ምርጫ አላቸው። ወደ ኢስላም የሚደረግን ዳዕዋ በመከልከል ላይ የሙጥኝ ካሉ ግን በኢስላም ህግጋት መሰረት እነርሱን ከመጋደል ውጪ ሌላ ምንም አማራጭ አይኖርም።
ተጨማሪ