عن جابر رضي الله عنه:
أَنَّ رَجُلًا سَأَلَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: أَرَأَيْتَ إِذَا صَلَّيْتُ الصَّلَوَاتِ الْمَكْتُوبَاتِ، وَصُمْتُ رَمَضَانَ، وَأَحْلَلْتُ الْحَلَالَ، وَحَرَّمْتُ الْحَرَامَ، وَلَمْ أَزِدْ عَلَى ذَلِكَ شَيْئًا، أَأَدْخُلُ الْجَنَّةَ؟ قَالَ: «نَعَمْ»، قَالَ: وَاللهِ لَا أَزِيدُ عَلَى ذَلِكَ شَيْئًا.
[صحيح] - [رواه مسلم]
المزيــد ...
ከጃቢር አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው፦
አንድ ሰውዬ የአላህን መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- "c2">“ እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ (ከተቀበልኩ) ከቆጠርኩና በዛም ላይ ምንም ካልጨመርኩ ጀነት እገባለሁን?” ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "c2">“አዎን!” አሉት። እሱም፦ "በዚህ ላይ አንድንም ላልጨምር በአላህ እምላለሁ! " አለ።
Sahih/Authentic. - [Muslim]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አምስቱን ግዴታ ሰላቶች የሰገደና አንድም ተጨማሪ ሰላት ጨምሮ ያልሰገደ ፣ ረመዳንን የፆመና ሱና ፆሞችን ያልፆመ፣ (ሐላል) ፍቁድ ነገሮችን በፍቁድነታቸው አምኖ የተገበረና ሐራም ነገሮችን በክልክልነታቸው አምኖ የራቀ ጀነት እንደሚገባ ይገልጻሉ።