+ -

عَنْ أَسْمَاءَ بِنْتِ أَبِي بَكْرٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا، قَالَتْ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِنِّي عَلَى الحَوْضِ حَتَّى أَنْظُرَ مَنْ يَرِدُ عَلَيَّ مِنْكُمْ، وَسَيُؤْخَذُ نَاسٌ دُونِي، فَأَقُولُ: يَا رَبِّ مِنِّي وَمِنْ أُمَّتِي، فَيُقَالُ: هَلْ شَعَرْتَ مَا عَمِلُوا بَعْدَكَ، وَاللَّهِ مَا بَرِحُوا يَرْجِعُونَ عَلَى أَعْقَابِهِمْ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6593]
المزيــد ...

አስማእ ቢንት አቢበክር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"እኔ ሐውድ (ኩሬ) ላይ ሁኜ ከናንተ መካከል ወደ እኔ የሚመጣን እመለከታለሁ። በአቅራቢያዬ ያሉ ሰዎች (እንዳይጠጡ) ይያዛሉ። እኔም "ጌታዬ ከኔ ከኡመቴ ናቸው’እኮ" እላለሁ። ለኔም፦ "ከአንተ ህልፈት በኋላ የሠሩትን ታውቃለህን? በአላህ እምላለሁ (ከእምነታቸው) ወደ ኋላ ከማፈግፈግ አልተወገዱም።" እባላለሁ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6593]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የትንሳኤ ቀን ከኡመታቸው መካከል ወደ ኩሬያቸው የሚመጣን ሰው ለመመልከት ከኩሬያቸው ላይ እንደሚሆኑ ገለፁ። ከሳቸው አቅራቢያም ሰዎች እንዳይጠጡ ይያዛል። እርሳቸውም፦ "ጌታዬ ሆይ እነሱ ከኔ ኡመት እኮ ናቸው" ይላሉ። ለርሳቸውም፦ "አንተን ከተለያዩ በኋላ የሰሩትን ታውቃለህን? በአላህ እምላለሁ ወደኋላቸው ከመመለስና ከእምነታቸው ከማፈንገጥ አልተወገዱም። ከአንተም አይደሉም ከኡመትህም አይደሉም።" ተብሎ ይመለስላቸዋል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለኡመታቸው ያላቸው እዝነትና ስለ ተከታዮቻቸው ያላቸው ጉጉት፤
  2. ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የነበሩበትን መንገድ መቃረን አደገኝነት፤
  3. የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሱና አጥብቆ በመያዝ ላይ መነሳሳቱን ተረድተናል።