+ -

عَنْ أَبِي ذَرٍّ رضي الله عنه قَالَ:
قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ مَا آنِيَةُ الْحَوْضِ؟ قَالَ: «وَالَّذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ لَآنِيَتُهُ أَكْثَرُ مِنْ عَدَدِ نُجُومِ السَّمَاءِ وَكَوَاكِبِهَا، أَلَا فِي اللَّيْلَةِ الْمُظْلِمَةِ الْمُصْحِيَةِ، آنِيَةُ الْجَنَّةِ مَنْ شَرِبَ مِنْهَا لَمْ يَظْمَأْ آخِرَ مَا عَلَيْهِ، يَشْخَبُ فِيهِ مِيزَابَانِ مِنَ الْجَنَّةِ، مَنْ شَرِبَ مِنْهُ لَمْ يَظْمَأْ، عَرْضُهُ مِثْلُ طُولِهِ، مَا بَيْنَ عَمَّانَ إِلَى أَيْلَةَ، مَاؤُهُ أَشَدُّ بَيَاضًا مِنَ اللَّبَنِ، وَأَحْلَى مِنَ الْعَسَلِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2300]
المزيــد ...

አቡ ዘር -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦
"የአላህ መልክተኛ ሆይ! የኩሬው መጠጫ እቃ ምንድነው?" አልኳቸው። "የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! መጠጫ እቃው ከሰማይ ከዋክብት ቁጥር የበዛ ነው። ንቁ! ይህም ከደመና የፀዳ የሌሊት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ከሚታዩት የከዋክብት ቁጥር የበዛ ነው። የጀነት እቃ ነው። ከእርሱ የጠጣም ለመጨረሻ ጊዜ ከነበረበት ጥም ውጪ አይጠማም። ከጀነት የሆኑ ሁለት አሸንዳዎች ወደ ኩሬው ውኃን ያንቧቧሉ። ከሱ የጠጣ መቼም አይጠማም። የጎኑ ስፋት እንደ አግድመቱ ከዐማን እስከ አይለህ ይደርሳል። ውኃው ከወተት እጅግ የነጣ ከማር እጅግ የጣፈጠ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2300]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የትንሳኤ ቀን የምንጫቸው መጠጫ እቃ ከሰማይ ኮኮቦች ቁጥር እንደሚበዛ ማሉ። ይህ የሰማይ ከዋክብት ቁጥርም ጨረቃ በሌለበት ድቅድቅ ምሽት ወቅት ግልፅ ይሆናል። ምክንያቱም ጨረቃ ባበራችበት ምሽት ኮኮቦች በጨረቃዋ ብርሃን ስለሚሸፈኑ ግልፅ አይሆኑም። እንዲሁም ደመና በሌለበትም ምሽት ወቅት ነው። ምክንያቱም የደመና መኖር ኮኮቦችን ከመታየት ይከለክላል። ከጀነት እቃ ውስጥ መጠጥን የጠጣ መቼም አይጠማም። ይህም አንድ ጠጪን የሚያጋጥመው የመጨረሻ ጥም ይሆናል። ከጀነት ሁለት አሸንዳዎች ወደ ኩሬያቸው ይፈሳል። የምንጫቸው አግድመቱ የእርዝማኔው አምሳያ ነው። የኩሬያቸው ማእዘናት እኩኩል ነው። እርዝማኔው ከዐማን (ሻም ውስጥ የምትገኝ በልቃእ የምትባል ሀገር ናት።) እስከ አይለህ (በሻም ጫፍ የምትገኝ የታወቀች ከተማ ናት።) የሚደርስ ርቀት ያክል ነው። የኩሬያቸው ውኃ ከወተት እጅግ የበዛ ንጣት ያለው ሲሆን ጣእሙም ከማር ጣእም ጥፍጥና የበለጠ እጅግ ጣፋጭ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht Azerisht الأوزبكية الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሐውድን (ኩሬ) እና በውስጡ ያለውን የተለያዩ ፀጋዎች ማፅደቅ፤
  2. የኩሬያቸው ግዝፈት፣ እርዝማኔውና ጎኑን፣ የመጠጫ እቃዎቹን መብዛት አውቀናል።