+ -

عَنْ أَنَسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ:
أَنَّ رَجُلًا سَأَلَ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنِ السَّاعَةِ، فَقَالَ: مَتَى السَّاعَةُ؟ قَالَ: «وَمَاذَا أَعْدَدْتَ لَهَا». قَالَ: لاَ شَيْءَ، إِلَّا أَنِّي أُحِبُّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: «أَنْتَ مَعَ مَنْ أَحْبَبْتَ». قَالَ أَنَسٌ: فَمَا فَرِحْنَا بِشَيْءٍ، فَرِحْنَا بِقَوْلِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «أَنْتَ مَعَ مَنْ أَحْبَبْتَ» قَالَ أَنَسٌ: فَأَنَا أُحِبُّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَأَبَا بَكْرٍ، وَعُمَرَ، وَأَرْجُو أَنْ أَكُونَ مَعَهُمْ بِحُبِّي إِيَّاهُمْ، وَإِنْ لَمْ أَعْمَلْ بِمِثْلِ أَعْمَالِهِمْ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3688]
المزيــد ...

ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ ትንሳኤ እለት ጠየቃቸው። "ትንሳኤ መቼ ነው?" አላቸው። እርሳቸውም "ለርሷ ምን አዘጋጅተሀል?" አሉት። እርሱም "እኔ አላህና መልክተኛውን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመውደዴ ውጭ ምንም ነገር አላዘጋጀሁም።" አለ። እርሳቸውም "አንተ ከወደድካቸው ጋር ነህ።" አሉት። አነስም እንዲህ አሉ፦ "በዚህ "አንተ ከወደድካቸው ጋር ነህ።" በሚለው የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግር እንደተደሰትነው በምንም አልተደሰትንም።" ቀጥሎም (አነስ) እንዲህ አሉ: "እኔ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና)፣ አቡበከርንና ዑመርን እወዳለሁ። እነርሱ የሰሩትን አምሳያ ባልሰራ እንኳ እነርሱን በመውደዴ ከነርሱ ጋር መሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3688]

ትንታኔ

አንድ የገጠር ሰው ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ትንሳኤ ስለምትከሰትበት ወቅት ጠየቃቸው።
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ: ለርሷ ከመልካም ስራ ምን አዘጋጅተህላታል? አሉት።
ጠያቂውም: እኔ አላህና መልክተኛውን እወዳለሁ እንጂ ትልቅ ስራ አላዘጋጀሁላትም አለ። ከዚህ በቀር የቀልብም፣ የአካልም ሆነ የገንዘብ አምልኮ አላወሳም። እነዚህ ሁሉ ውዴታን ተከትሎ የሚመጡ ቅርንጫፎች ናቸውና። ለመልካም ስራ የሚያነሳሳውም እውነተኛ ውዴታ ስለሆነ ነው።
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ: አንተ ጀነት ውስጥ ከወደድካቸው ጋር ነህ አሉት።
የነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶሐቦች በዚህ ብስራት ከፍተኛ ደስታን ተደሰቱ።
አነስም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ቀጥሎ ስራው እንደነርሱ አምሳያ ባይሆንም እንኳ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና)፣ አቡበከርንና ዑመርን ስለሚወድ ከነርሱ ጋር መሆንንም ተስፋ እንደሚያደርግ ተናገረ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الدرية الصربية الرومانية Malagasisht Oromisht Kannadisht الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለጠያቂ መልስ ሲሰጡ የተጠቀሙትን ጥበብ እንረዳለን። ለጠያቂው አንገብጋቢውንና የሚያድነው የሆነውን ጉዳይ ጠቆሙት። እርሱም: በሚጠቅም መልካም ስራ ለመጪው አለም መዘጋጀት ነው።
  2. ሰው አላህን ለመገናኘት ተዘጋጅቶና ተሰናድቶ እንዲኖር አላህ የትንሳኤን ቀን እውቀት ከባሮቹ ላይ ደበቀው።
  3. አላህን፣ መልክተኞችን፣ አማኝ የሆኑ ደጋጎችን የመውደድን ትሩፋትና አጋርያንን ከመውደድ መጠንቀቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
  4. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና): አንተ ከወደድካቸው ጋር ነህ ማለታቸው በደረጃና በማዕረግ እኩል መሆንን አይጠቁምም። ይልቁኑም የተፈለገው ምንም ቢራራቁ ራሱ አንዱ ሌላውን መመልከት በሚችልበት መልኩ በጀነት ውስጥ እንደሚሆኑ ነው።
  5. ሙስሊምን እጅግ በሚጠቅመውና በሚበጀው ጉዳይ እንዲጠመድና ስለማይጠቅመው ነገር ከመጠየቅ እንዲተው መጠቆም እንደሚገባ እንረዳለን።
ተጨማሪ