عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«أَمَا يَخْشَى أَحَدُكُمْ - أَوْ: لاَ يَخْشَى أَحَدُكُمْ - إِذَا رَفَعَ رَأْسَهُ قَبْلَ الإِمَامِ، أَنْ يَجْعَلَ اللَّهُ رَأْسَهُ رَأْسَ حِمَارٍ، أَوْ يَجْعَلَ اللَّهُ صُورَتَهُ صُورَةَ حِمَارٍ».
[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"አንዳችሁ ከኢማም በፊት ጭንቅላቱን ቀና ያደረገ ጊዜ አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት እንዳያደርገው ወይም አላህ የሰውነት ቅርፁን የአህያ የሰውነት ቅርፅ እንዳያደርግበት አይፈራምን?!"
Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጭንቅላቱን ከኢማሙ በፊት ቀና የሚያደርግ ሰው አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት ሊያደርግበት ወይም የሰውነት ቅርፁን የአህያ ቅርፅ ሊያደርግበት እንደሚችል በመግለፅ ከባድ ዛቻን አስተላለፉ።