عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«سَوُّوا صُفُوفَكُمْ، فَإِنَّ تَسْوِيَةَ الصَّفِّ مِنْ تَمَامِ الصَّلَاةِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 433]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ሰልፋችሁን አስተካክሉ! ሰልፍ ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉት መካከል ነውና።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 433]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰጋጆች ሰልፋቸውን እንዲያስተካክሉ፤ ከፊላቸው ከከፊሉ እንዳይቀደምና እንዳይዘገይ አዘዙ። ሰልፍን ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉ ምክንያቶች አንዱ ሲሆን የሰልፍ መጣመምም ሶላት ውስጥ ጉድለትና ክፍተት የሚያስከትል መሆኑን ገለፁ።