+ -

عَنْ ‌مَحْمُودِ بْنِ لَبِيدٍ رضي الله عنه:
أَنَّ ‌عُثْمَانَ بْنَ عَفَّانَ أَرَادَ بِنَاءَ الْمَسْجِدِ فَكَرِهَ النَّاسُ ذَلِكَ، وَأَحَبُّوا أَنْ يَدَعَهُ عَلَى هَيْئَتِهِ، فَقَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ: «مَنْ بَنَى مَسْجِدًا لِلهِ بَنَى اللهُ لَهُ فِي الْجَنَّةِ مِثْلَهُ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 533]
المزيــد ...

ከመሕሙድ ቢን ለቢድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
"ዑሥማን ቢን ዐፋን (የነቢዩን) መስጂድ መገንባት ፈለጉ። ይህንንም ሰዎች ጠሉ። ባለበት እንዲተወውም ፈለጉ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: 'የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: ‹ ለአላህ ብሎ መስጂድን የገነባ አላህም ለርሱ አምሳያውን ጀነት ውስጥ ይገነባለታል።›' አለ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 533]

ትንታኔ

ዑሥማን ቢን ዐፋን አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂዱ መጀመሪያ ከነበረበት ባማረ መልኩ አድሶ መገንባት ፈለጉ። ሰዎችም መስጂዱ በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘመን ከነበረበት ሁኔታ ስለሚለወጥ ይህንን የዑሥማን ሀሳብ ጠሉ። የመስጂዱ ግድግዳ በጡብ የተገነባ ሲሆን ጣሪያው በዘንባባ ቅጠል ነበር የተሰራው። ዑሥማን ግን በድንጋይና በጀሶ ነበር መገንባት የፈለጉት። በዚህ ጊዜ ዑሥማን (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ለይዩልኝና ይስሙልኝ ሳይሆን የአላህን ውዴታ ፈልጎ መስጂድ የገነባ አላህ በስራው አይነት የበለጠ ምንዳ ይመነዳዋል። ይህም ምንዳ በገነባው ቤት አምሳያ አሏህም ለርሱ ጀነት ውስጥ የሚገነባለት መሆኑ ነው።" ሲሉ መስማታቸውን ነገሯቸው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. መስጂዶችን በመገንባት ላይ መነሳሳቱና የዚህንም ትሩፋት እንረዳለን።
  2. መስጂድን ማስፋትና ማደስ የመገንባት ትሩፋት ውስጥ ይካተታል።
  3. በሁሉም ስራዎች ስራን ለአላህ ማጥራት አንገብጋቢነቱን እንረዳለን።