عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«سَبْعَةٌ يُظِلُّهُمُ اللَّهُ تَعَالَى فِي ظِلِّهِ يَوْمَ لاَ ظِلَّ إِلَّا ظِلُّهُ: إِمَامٌ عَدْلٌ، وَشَابٌّ نَشَأَ فِي عِبَادَةِ اللَّهِ، وَرَجُلٌ قَلْبُهُ مُعَلَّقٌ فِي المَسَاجِدِ، وَرَجُلاَنِ تَحَابَّا فِي اللَّهِ، اجْتَمَعَا عَلَيْهِ وَتَفَرَّقَا عَلَيْهِ، وَرَجُلٌ دَعَتْهُ امْرَأَةٌ ذَاتُ مَنْصِبٍ وَجَمَالٍ فَقَالَ: إِنِّي أَخَافُ اللَّهَ، وَرَجُلٌ تَصَدَّقَ بِصَدَقَةٍ فَأَخْفَاهَا حَتَّى لاَ تَعْلَمَ شِمَالُهُ مَا تُنْفِقُ يَمِينُهُ، وَرَجُلٌ ذَكَرَ اللَّهَ خَالِيًا، فَفَاضَتْ عَيْنَاهُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1423]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ሰባት አካላቶች ከአላህ ጥላ በቀር ጥላ በሌለበት ቀን አላህ በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል። ፍትሃዊ መሪ፤ አላህን በማምለክ ያደገ ወጣት፤ ቀልቡ ወደ መስጂዶች የተንጠለጠለ ሰውዬ፤ በአላህ መንገድ የተገናኙ በርሱም መንገድ የተለያዩ ለአላህ ብለው የተዋደዱ ሁለት ሰዎች፤ የተከበረችና ቆንጆ የሆነች ሴት ለዝሙት ጠርታው እኔ አላህን እፈራለሁ ያለ ሰውዬ፤ ቀኙ የምትሰጠውን ግራው እስከማታውቅ ድረስ ምፅዋቱን በመደበቅ ምፅዋት የመፀወተ ሰውዬ፤ አላህን ገለል ብሎ አውስቶ አይኖቹ ያነቡ ሰውዬ ናቸው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1423]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከአማኞች ሰባት አይነት ሰዎችን ከአላህ ጥላ ውጪ ሌላ ጥላ በሌለበት ቀን አላህ ከዐርሹ ጥላ ስር እንደሚያስጠልላቸው አበሰሩ። አንደኛ: ወንጀለኛ ባለመሆን በራሱ ላይ ፍትሃዊ የሆነ፤ የሚመራቸውንም ህዝቦች ባለመበደል በህዝቦቹ መካከል ፍትሃዊ የሆነ መሪ ነው። ይህም ትልቅ ስልጣን የተሸከመ ሰው ነው። በተመሳሳይም የሙስሊሞችን ጉዳይ የሚመራ ፍትሃዊ የሆነ ሰው ሁሉ እዚህ ውስጥ ይካተታል። ሁለተኛ: አላህን በማምለክ ያደገ ወጣት፤ እስኪሞት ድረስም ወጣትነቱንና የንቃት እድሜውን በዚሁ ሁኔታ የጨረሰ ሰው ነው። ሶስተኛ: ቀልቡ ወደ መስጂድ የተንጠለጠለ ሰውዬ ነው። መስጂድን በደንብ ስለሚወድና አብዝቶ መስጂድ ውስጥ ስለሚያሳልፍ ከመስጂድ በወጣ ቁጥር ወደ መስጂድ እስኪመለስ ድረስ ይጓጓል። ከመስጂድ ውጪ ሆኖ አካሉ የሆነ ነገር ቢያጋጥመው እንኳ ቀልቡ መስጂድ ላይ እንደሆነ የሚቀጥል ነው። አራተኛ: በትክክል ለአላህ ብለው የተዋደዱ ሁለት ሰዎች በእምነታዊ ውዴታ ላይ ሆነውም የዘወተሩ፤ በአካል ወይም በርቀት ባይገናኙ እንኳ በመካከላቸው ሞት እስኪለያያቸው ድረስ በአለማዊ ጉዳይ ያልተቆራረጡ ናቸው። አምስተኛ: የጥሩ ዘር፣ የልቅና፣ የክብር፣ የገንዘብ፣ የቁንጅና ባለቤት የሆነች ሴት ከርሷ ጋር ዝሙት እንዲፈፅም ፈልጋው እኔ አላህን እፈራለሁ በማለት እምቢ ያለ ሰውዬ ነው። ስድስተኛ: ቀኙ የምትሰጠውን ግራው እስከማታውቅ ድረስ በመደበቅና ይዩልኝ ውስጥ ሳይገባ ትንሽም ይሁን ብዙ ምፅዋትን የመፀወተ ሰው ነው። ሰባተኛ: ከሰዎች ገለል ብሎ አላህን በቀልቡ በማስታወስ ወይም በምላሱ ዚክር በማለት ያወሳና አላህን በመፍራትና በማላቅ ሁለት አይኖቹ ያነቡ ሰው ነው።