عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِنَّ اللهَ يَرْضَى لَكُمْ ثَلَاثًا، وَيَكْرَهُ لَكُمْ ثَلَاثًا، فَيَرْضَى لَكُمْ: أَنْ تَعْبُدُوهُ، وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا، وَأَنْ تَعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا، وَيَكْرَهُ لَكُمْ: قِيلَ وَقَالَ، وَكَثْرَةَ السُّؤَالِ، وَإِضَاعَةِ الْمَالِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1715]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ ለናንተ ሶስት ነገር ይወድላችኋል፤ ሶስት ነገርንም ይጠላባችኋል። እርሱን መገዛታችሁን፣ በርሱ ላይ አንዳችንም አለማጋራታችሁን፣ ሁላችሁም በአላህ ገመድ መተሳሰራችሁንና አለመለያየታችሁን ለናንተ ይወድላችኋል። አሉባልታን፣ ጥያቄ ማብዛትንና ገንዘብ ማባከንን በናንተ ላይ ይጠላባችኋል።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1715]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላህ ባሮቹ ላይ ሶስት ነገሮችን እንደሚወድና በነርሱ ላይም ሶስት ነገር እንደሚጠላባቸው ተናገሩ። በነርሱ ላይ የሚወደው: እርሱን በአምልኮ መነጠላቸው፤ በርሱ ላይ አንዳችንም አለማጋራታቸው፤ በአላህ ቃልኪዳን፣ በቁርአንና በነቢዩ ሱና አንድ ላይ መተሳሰራቸውንና ከሙስሊሙ ህብረት አለመለያየታቸውን ነው። በነርሱ ላይ የሚጠላውም: የማይጠቅማቸውን ትርፍና ዛዛታ ንግግር መናገራቸውን፤ ስላልተከሰተ ነገር መጠየቅ ወይም ሰዎችን ገንዘብ እንዲሰጧቸው፣ በእጃቸው የያዙትን እንዲሰጧቸውና ያላስፈለጋቸውን ነገር መጠየቅ፤ ገንዘብን ማጥፋት፣ ከሸሪዓዊ አላማው ውጪ ለሆነ ጉዳይ ማዋልና ለጥፋት መዳረግ ናቸው።