عَن أَبي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لاَ يُشِيرُ أَحَدُكُمْ عَلَى أَخِيهِ بِالسِّلاَحِ، فَإِنَّهُ لاَ يَدْرِي، لَعَلَّ الشَّيْطَانَ يَنْزِعُ فِي يَدِهِ، فَيَقَعُ فِي حُفْرَةٍ مِنَ النَّارِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 7072]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
"አንዳችሁ ወንድሙ ላይ መሳሪያን አይደቅን። አይታወቅም ምናልባት ሸይጧን መሳሪያውን ከእጁ ላይ ይወሰውሰውና በእሳት ጉድጓድ ውስጥ ሊጥለው ይችላልና።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 7072]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ሙስሊም ወደ ሙስሊም ወንድሙ ማንኛውንም የመሳሪያ አይነት ከመደቀን አስጠነቀቁ። ምናልባት ሳይታወቀው እጁ ላይ ባለው መሳሪያው ሸይጧን ወስውሶት ወንድሙን እንዲገድል ወይም እንዲጓዳ ሊያደርገው ይችላልና። በዚህም የእሳት ጉድጓድ ውስጥ ወደ ለመጣል የሚያደርሰው ወንጀል ላይ ይወድቃል።