عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ تَرَدَّى مِنْ جَبَلٍ فَقَتَلَ نَفْسَهُ فَهُوَ فِي نَارِ جَهَنَّمَ يَتَرَدَّى فِيهِ خَالِدًا مُخَلَّدًا فِيهَا أَبَدًا، وَمَنْ تَحَسَّى سُمًّا فَقَتَلَ نَفْسَهُ فَسُمُّهُ فِي يَدِهِ يَتَحَسَّاهُ فِي نَارِ جَهَنَّمَ خَالِدًا مُخَلَّدًا فِيهَا أَبَدًا، وَمَنْ قَتَلَ نَفْسَهُ بِحَدِيدَةٍ فَحَدِيدَتُهُ فِي يَدِهِ يَجَأُ بِهَا فِي بَطْنِهِ فِي نَارِ جَهَنَّمَ خَالِدًا مُخَلَّدًا فِيهَا أَبَدًا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5778]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ነፍሱን ከተራራ ላይ ጥሎ የገደለ ሰው በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ሲምዘገዘግ ይኖራል። መርዝ ጠጥቶ ነፍሱን የገደለ ሰው በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ መርዙን በእጁ ይዞ ሲጠጣው ይቆያል። ነፍሱን በስለት የገደለ ሰውም በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ስለቱን በእጁ ይዞ ሆዱን እየወጋበት ይኖራል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5778]
ነቢዩ(የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በዱንያ ውስጥ ሆን ብሎ ራስን ከማጥፋት አስጠነቀቁ። ይህን የፈፀመ ሰው የትንሳኤ ቀን በጀሃነም እሳት ውስጥ ነፍሱን በዱንያ በገደለበት መልኩ ራሱን ይቀጣል። ይህም ተስማሚ ቅጣት ነው። ነፍሱን ከተራራ ላይ ጥሎ የገደላት በጀሃነም እሳት ውስጥ ከሚገኝ ተራራ ወደ ጀሃነም ሸለቆዎች ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ነፍሱን በመጣል ራሱን ይቀጣል። መርዝ ጠጥቶ ነፍሱን የገደለ ሰውም በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ መርዙን በእጁ ይዞ ይጠጣዋል። ነፍሱን በስለት የገደለ ሰው በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ስለቱን በእጁ ይዞ በርሱ ሆዱን እየወጋ ይኖራል።