عَنِ ابْنِ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَنْ يَزَالَ المُؤْمِنُ فِي فُسْحَةٍ مِنْ دِينِهِ، مَا لَمْ يُصِبْ دَمًا حَرَامًا».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6862]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዓንሁማ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል
"አማኝ የሆነ ሰው ክልክል የሆነን ደም እስካላፈሰሰ ድረስ በሃይማኖቱ ነፃነት ውስጥ ከመሆን አይወገድም።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6862]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አማኝ የሆነ ሰው በመልካም ስራዎቹ ላይ ነፃነትና የአላህ እዝነት፣ ምህረትና ይቅርታው ውስጥ ከመሆን እንደማይወገድ ተናገሩ። መግደሉ ክልክል የሆነን ሰው የገደለ ጊዜ ግን ስራው የግድያውን ወንጀልና ይህን ትልቅ ወንጀሉን ስለማትሸፍን ስራው ትጠብበታለች።