+ -

عن خَولة الأنصاريةِ رضي الله عنها قالت: سمعت النبي صلى الله عليه وسلم يقول:
«إِنَّ رِجَالًا يَتَخَوَّضُونَ فِي مَالِ اللهِ بِغَيْرِ حَقٍّ، فَلَهُمُ النَّارُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 3118]
المزيــد ...

ከኸውለህ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:
"በአላህ ገንዘብ ያለአግባብ የሚገለገሉ ሰዎች ለነርሱ የትንሳኤ ቀን እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3118]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሙስሊሞችን ገንዘብ ያለአግባብ ስለሚጠቀሙና ያለአግባብ ስለሚበዘብዙ ሰዎች ተናገሩ። ይህም ገንዘብን ባልተፈቀደ መልኩ ማጠራቀምና ማግኘትን እንዲሁም ትክክለኛ ባልሆነ ቦታ ፈሰስ ማድረግን የሚጠቀልል ሀሳብ ነው። የየቲሞችን ገንዘብ መብላት፣ ወቅፍ የተደረገን ገንዘብ መብላት፣ አደራዎችን መካድ፣ የማህበረሰቡን ገንዘብ ያለአግባብ መውሰድ ሁሉ እዚህ ውስጥ ይካተታል።
ቀጥለውም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የትንሳኤ ቀን የነዚህ ሰዎች ምንዳ እሳት መሆኑን ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በሰዎች እጅ ያሉ ገንዘቦች እሱ በደነገገላቸው መንገድ እንዲያወጡትና ያለአግባብ ከመገልገል ይርቁ ዘንድ ሰዎችን ምትክ ያደረገበት የአሏህ ገንዘቡ ነው። ይህም መሪዎችንም ሆነ ሌሎችንም አጠቃላይ ሰዎችን የሚጠቀልል ነው።
  2. ሸሪዓ በማህበረሰቡ ገንዘብ ዙሪያ ጥብቅ መሆኑን እንረዳለን። ከገንዘብ በጥቂቱም ቢሆን የተሾመ ሰው የትንሳኤ ቀን ስለገንዘቡ አሰባሰብም ሆነ ስለአወጣጡ ይተሳሰባል።
  3. የራሱንም ገንዘብ ሆነ የሌላውን ገንዘብ ሸሪዓዊ ባልሆነ መልኩ የሚገለገልም በዚህ ዛቻ ይካተታል።