عن عائشة رضي الله عنها قالت: سمعتُ من رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول في بيتي هذا:
«اللَّهُمَّ مَنْ وَلِيَ مِنْ أَمْرِ أُمَّتِي شَيْئًا فَشَقَّ عَلَيْهِمْ فَاشْقُقْ عَلَيْهِ، وَمَنْ وَلِيَ مِنْ أَمْرِ أُمَّتِي شَيْئًا فَرَفَقَ بِهِمْ فَارْفُقْ بِهِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1828]
المزيــد ...
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: የአላህ መልክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቴ ውስጥ ይህንን ሲሉ ሰምቻለሁ:
"አላህ ሆይ! ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና እነርሱን ለችግር የዳረገ እርሱንም የሚቸገር አድርገው ። ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና ለነሱ የራራን ለርሱም ራራለት።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1828]
የሙስሊሞች ጉዳዮች ውስጥ በየትኛውም ትንሽም ይሁን ትልቅ ሹመት ፣ አጠቃላይም ይሁን ቁንፅል ሹመትን የተሾመ ከዚያም ለሙስሊሞች ሳይራራ ችግርን በነርሱ ላይ የሚያባብስባቸው የሆነን ሰው ሁሉ ላይ አላህ በሰራው ስራ ተመሳሳይ እሱንም ለችግር እንዲዳርገው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዱዓእ አደረጉበት።
ለነርሱ የራራና ጉዳዮቻቸውን ባቀለለ ላይም አላህ ለርሱ እንዲራራና ጉዳዮቹን እንዲያገራለት ዱዓ አደረጉለት።