عن مَعقِلِ بن يَسار المُزَنِيّ رضي الله عنه قال: إني سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«مَا مِنْ عَبْدٍ يَسْتَرْعِيهِ اللهُ رَعِيَّةً، يَمُوتُ يَوْمَ يَمُوتُ وَهُوَ غَاشٌّ لِرَعِيَّتِهِ، إِلَّا حَرَّمَ اللهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 142]
المزيــد ...
ከመዕቂል ቢን የሳር አልሙዘኒይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: እኔ የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:
"አላህ አንድ ሀላፊነት ላይ ሹሞት የተሰጠውን ሀላፊነት የሚያታልል ሆኖ የሚሞት ባሪያ የለም አላህ በርሱ ላይ ጀነትን እርም የሚያደርግ ቢሆን እንጂ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 142]
እያንዳንዱ አላህ በሰዎች ላይ ተጠያቂና ሀላፊ ያደረገው ሁሉ እንደመሪነት ጠቅላይ ሀላፊነትን የሚያስተዳድርም ይሁን ወይም በቤቱ ሀላፊ እንደሆነ ወንድና በቤቷ ሀላፊ እንደሆነች ሴት ውስን ሀላፊነትም ይሁን የሀላፊነት ግዴታውን ካጓደለ፣ ቅን ሳይሆን ካጭበረበረና ዲናዊና ዓለማዊ ግዴታውን ካጠፋ ለከባድ ቅጣት እንደተገባ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።