+ -

عن عُبَادَةَ بن الصَّامتِ رضي الله عنه قال:
بَايَعْنَا رسولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم على السَّمْعِ وَالطَّاعَةِ فِي الْعُسْرِ وَالْيُسْرِ، وَالْمَنْشَطِ وَالْمَكْرَهِ، وعلى أَثَرَةٍ علينا، وعلى أَلَّا نُنَازِعَ الْأَمْرَ أهلَه، وعلى أَنْ نَقُولَ بِالْحَقِّ أينما كُنَّا، لا نَخَافُ في الله لَوْمَةَ لَائِمٍ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1709]
المزيــد ...

ከዑባዳህ ቢን ሷሚት (ረዲየላሁ ዐንሁ) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው እንዲህ አለ፦
"ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር መሪያችንን በችግርም ጊዜ ሆነ በድሎት ፣ በንቃትም ጊዜ ሆነ በጠላንበትም ጊዜ ፣ በኛ ላይ አድሎ ቢደረግብንም እንኳ እንድንሰማውና እንድንታዘዘው፤ የስልጣን ባለቤትም በጉዳዩ ከአላህ ግልፅ ማስረጃ የመጣበትን ግልፅ ክህደት እስካላያችሁበት ድረስ (ስልጣኑን) ላንጋፋው፣ የትም ብንሆን እውነትን እንድንናገር ፣ በአላህ መንገድም የወቃሽን ወቀሳ ላንፈራ ቃል ተጋብተናል።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1709]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሶሐቦች ጋር ለመሪዎችና አስተዳዳሪዎች በገርም ይሁን በከባድ፣ በሀብትም ይሁን በድህነት ወቅት፣ ትእዛዞቻቸው ነፍስ የምትወደውም ሆነ የምትጠላው ለነርሱ ታዛዥ እንዲሆኑ ቃል ኪዳን ፈፀሙ። መሪዎች በህዝብ አጠቃላይ ገንዘብ ወይም በማእረግ ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ ነገሮች አድሎ ቢፈፅሙ እንኳ መሪዎችን በመልካም መታዘዝና መስማት ግዴታ መሆኑንና እነርሱንም አምፀው ላይወጡ ቃል ኪዳን ፈፀሙ። ምክንያቱም መሪዎችን በመዋጋት የሚመጣው ፈተናና ብልሽት በግፋቸው ሳቢያ ከሚከሰተው ብልሽት እጅግ የገዘፈ ነውና። በንግግራቸው ለአላህ ብቻ ያጠሩ (ሙኽሊስ) ሲሆኑና ወቃሻቸውን ሳይፈሩ እውነትን በማንኛውም ስፍራ መናገርም ሌላው ቃል ኪዳን የተጋቡት ጉዳይ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. መሪዎችን የመስማትና የመታዘዝ ዋናው ጥቅም የሙስሊሞችን ቃል አንድ ማድረግና ልዩነትን ማስወገድ ነው።
  2. አላህን ከመወንጀል ውጪ በድሎትም ይሁን በችግር፣ በንቃትም ጊዜ ይሁን በጠላንበት፣ እኛ ላይ አድሎ በሚያደርጉብን ወቅትም ቢሆን መሪዎችን መስማትና መታዘዝ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  3. በአላህ ጉዳይ የወቃሽን ወቀሳ ሳንፈራ እውነትን የትም ብንሆን መናገር ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።