عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤْمِنين رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا، قَالَتْ:
مَا رَأَيْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مُسْتَجْمِعًا قَطُّ ضَاحِكًا، حَتَّى أَرَى مِنْهُ لَهَوَاتِهِ، إِنَّمَا كَانَ يَتَبَسَّمُ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6092]
المزيــد ...
ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
"የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንጥላቸውን እስክመለከት ድረስ በጭራሽ ሙሉ አፋቸውን ከፍተው ሲስቁ ተመልክቻቸው አላውቅም። ሲስቁ ፈገግ ብቻ ነበር የሚሉት"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6092]
ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሳቃቸው እንጥላቸው እስኪታይ ድረስ ከመጠን ያለፈ እንዳልነበር፤ ከሳቁም ፈገግ ብቻ ይሉ እንደነበር ተናገረች። እንጥል ማለት ከጉሮሮ በላይ የተንጠለጠለ ስጋ ነው።