قال سعد بن هشام بن عامر -عندما دخل على عائشة رضي الله عنها-:
يَا أُمَّ الْمُؤْمِنِينَ، أَنْبِئِينِي عَنْ خُلُقِ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، قَالَتْ: أَلَسْتَ تَقْرَأُ الْقُرْآنَ؟ قُلْتُ: بَلَى، قَالَتْ: فَإِنَّ خُلُقَ نَبِيِّ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ الْقُرْآنَ.

[صحيح] - [رواه مسلم في جملة حديثٍ طويلٍ]
المزيــد ...

ሰዕድ ቢን ሂሻም ቢን ዓሚር እናታችን ዓኢሻህ ዘንድ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- የገባ ወቅት እንዲህ አለ:
"የሙእሚኖች እናት ሆይ! ስለአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር ንገሪኝ! እሷም 'ቁርአን አትቀራምን?' አለችኝ። እኔም 'እንዴታ!' አልኩኝ። እሷም ' የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ስነምግባር ቁርአን ነበር።' አለችኝ።"

Sahih/Authentic. - [Muslim]

ትንታኔ

የአማኞች እናት የሆነችው ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- ስለነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር ተጠየቀች። ጠያቂውን ሁሉንም ምሉዕ ባህሪያት ወደ ሰበሰበው ወደ ተከበረው ቁርአን በመመለስ ጠቅላይ በሆነ ንግግር መለሰችለት። ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቁርአናዊውን ስነምግባር የተላበሱ ፤ ቁርአን ያዘዘውን ይፈፅሙ፣ ቁርአን የከለከለውን ደግሞ ይርቁ እንደነበር፤ የሳቸው ስነምግባር በቁርአን መስራት ፣ ድንበሩ ላይ መቆም፣ የቁርአንን አዳብ መላበስ ፣ ምሳሌዎቹንና ታሪኮቹን ማስተንተን ነበር ብላ መለሰችለት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ቁርአናዊ ስነምግባር በመላበሳቸው ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አርአያ ማድረግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር መሞገሱ። የሳቸው ስነምግባር ከወሕይ ምንጭ የተቀዳ ነውና።
  3. ቁርአን ለሁሉም የተከበሩ ስነምግባሮች ምንጭ መሆኑን እንረዳለን።
  4. ስነምግባር በኢስላም ሁሉንም የሃይማኖቱን ክፍሎች ያጠቃልላል፤ ይህም ትእዛዛትን በመፈፀምና ክልከላውን በመራቅ ነው።