عن عبد الله بن عمرو رضي الله عنهما أن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«الرَّاحِمُونَ يَرْحَمُهمُ الرَّحمنُ، ارحَمُوا أهلَ الأرضِ يَرْحْمْكُم مَن في السّماء».
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وأحمد] - [سنن أبي داود: 4941]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ:
"ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 4941]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነዚያ ለሌሎች የሚያዝኑ አዛኙ ጌታ ሁሉን ነገር በሰፋው እዝነቱ እንደሚያዝንላቸው ገለፁ። ይህም ከሰሩት ጋር የገጠመ ምንዳ ነው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጥለው በምድር ላይ ለሚኖር ለሰውም፣ ለእንስሳም፣ ለበራሪም ሆነ ለሌላ ማንኛውም አይነት ፍጡር ባጠቃላይ ማዘንን አዘዙ። የዚህ ምንዳም ከሰማያቱ በላይ ያለው አላህ ያዝንላቹሀል።