+ -

عن جابر رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«رَحِمَ اللهُ رَجُلًا سَمْحًا إِذَا بَاعَ، وَإِذَا اشْتَرَى، وَإِذَا اقْتَضَى».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 2076]
المزيــد ...

ከጃቢር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡
"ሲሸጥም፣ ሲገዛም ይሁን ያበደረውን ሲያስመልስ ገር የሆነን ሰው አሏህ ይዘንለት።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2076]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሲሸጥ ለስላሳ፣ ቸርና ለጋስ ለሆነ ሁሉ የአሏህን እዝነት እንዲያገኝ ዱዓእ አደረጉለት፤ ይህም ዋጋውን በማናር ገዥን አያጨናንቅም፤ ይልቁን በመልካም ምግባር የሚኗኗር ነው። ሲገዛም ለስላሳ፣ ቸርና ለጋስ ስለሆነ እቃውን በማሳነስና በማጣጣል ዋጋውን አያራክስም። ያበደረውን እዳ ሲያስመልስም ለስላሳ፣ ቸርና ለጋስ ስለሆነ ገንዘቡ እጅግ ያስፈለገውን ድሀ አያካብድበትም፤ ይልቁንም በእዝነትና ርህራሄ ይጠይቃል፤ ለተጨናነቀም የጊዜ ፋታ ይሰጣል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht Azerisht الأوزبكية الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በሰዎች መካከል ያለን መስተጋብር ማስተካከል ሸሪዓው ከሚፈልጋቸው ዋንኛ ተፈላጊ ጉዳዮች መካከል መሆኑ፤
  2. በሽያጭና በግዥም ይሁን በሌላም መስክ ከሰዎች ጋር ባለን መስተጋብር እጅግ ያማረውን ስነምግባር መላበስ የሚበረታታ መሆኑን እንረዳለን።