+ -

«رَغِمَ أَنْفُ، ثُمَّ رَغِمَ أَنْفُ، ثُمَّ رَغِمَ أَنْفُ»، قِيلَ: مَنْ؟ يَا رَسُولَ اللهِ قَالَ: «مَنْ أَدْرَكَ أَبَوَيْهِ عِنْدَ الْكِبَرِ، أَحَدَهُمَا أَوْ كِلَيْهِمَا فَلَمْ يَدْخُلِ الْجَنَّةَ».
[صحيح] - [رواه مسلم]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"አፍንጫው በአፈር ትታሽ (ይዋረድ) አሁንም አፍንጫው በአፈር ትታሽ (ይዋረድ) አሁንም አፍንጫው በአፈር ትታሽ (ይዋረድ)" "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማንን ነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ከወላጆቹ ሁለቱን ወይም አንዱን በእርጅና ወቅት አግኝቷቸው ጀነት ያልገባ ነው።" አሉ።

ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዱዓቸውን ጥግ ከማድረሳቸው የተነሳ አፍንጫውን አፈር ላይ እንደተደፋ ሰው በማድረግ በውርደት እንዲከናነብ ሶስት ጊዜ ረገሙት። የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማንን ነው የረገሙት? ተብለው ተጠየቁ።
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዳቸውን ወይም ሁለቱን ወላጆቹ በእርጅና ወቅት አግኝቶ እነርሱ ጀነት ለመግባቱ ሰበብ ያልሆኑት ነው አሉ። ይህም የሚሆነው ለነርሱ በጎ ባለማድረጉና ሐቃቸውን በመንፈጉ ምክንያት ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ السويدية القيرقيزية اليوروبا الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ለወላጆች በጎ ማድረግ በተለይ ባረጁና በደከሙ ወቅት ግዴታ መሆኑንና ከጀነት መግቢያ ሰበቦች መካከል አንዱ እንደሆነ እንረዳለን።
  2. የወላጆችን ሐቅ ማጓደል ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።