عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ:
كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَسِيرُ فِي طَرِيقِ مَكَّةَ، فَمَرَّ عَلَى جَبَلٍ يُقَالُ لَهُ جُمْدَانُ، فَقَالَ: «سِيرُوا هَذَا جُمْدَانُ، سَبَقَ الْمُفَرِّدُونَ» قَالُوا: وَمَا الْمُفَرِّدُونَ يَا رَسُولَ اللهِ؟ قَالَ: «الذَّاكِرُونَ اللهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2676]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመካ መንገድ ላይ እየተጓዙ ሳለ ጁምዳን በሚባል ተራራ ላይ ሲያልፉ እንዲህ አሉ: "ይህ ጁምዳን ነው ተጓዙ! ሙፈሪዶች ቀደሙ!" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሙፈሪዶች እነማን ናቸው?" አሉ። እርሳቸውም "አላህን በብዛት የሚያወሱ ወንዶችና ሴቶች ናቸው።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2676]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህን በብዛት የሚያወሱ ሰዎች እነርሱ የተነጠሉና በዘውታሪዋ ጀነት ውስጥ ከፍተኛን ደረጃ በማግኘት ሌሎችን የቀደሙ መሆናቸውን በመጥቀስ ደረጃቸውን ገለፁ። ከሌሎች ተራራ ተነጥሎ በሚገኘው የጁምዳን ተራራም መሰሏቸው።