عن أبي هريرة رضي الله عنه
عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فِيمَا يَحْكِي عَنْ رَبِّهِ عَزَّ وَجَلَّ، قَالَ: «أَذْنَبَ عَبْدٌ ذَنْبًا، فَقَالَ: اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي ذَنْبِي، فَقَالَ تَبَارَكَ وَتَعَالَى: أَذْنَبَ عَبْدِي ذَنْبًا، فَعَلِمَ أَنَّ لَهُ رَبًّا يَغْفِرُ الذَّنْبَ، وَيَأْخُذُ بِالذَّنْبِ، ثُمَّ عَادَ فَأَذْنَبَ، فَقَالَ: أَيْ رَبِّ اغْفِرْ لِي ذَنْبِي، فَقَالَ تَبَارَكَ وَتَعَالَى: عَبْدِي أَذْنَبَ ذَنْبًا، فَعَلِمَ أَنَّ لَهُ رَبًّا يَغْفِرُ الذَّنْبَ، وَيَأْخُذُ بِالذَّنْبِ، ثُمَّ عَادَ فَأَذْنَبَ، فَقَالَ: أَيْ رَبِّ اغْفِرْ لِي ذَنْبِي، فَقَالَ تَبَارَكَ وَتَعَالَى: أَذْنَبَ عَبْدِي ذَنْبًا، فَعَلِمَ أَنَّ لَهُ رَبًّا يَغْفِرُ الذَّنْبَ، وَيَأْخُذُ بِالذَّنْبِ، اعْمَلْ مَا شِئْتَ فَقَدْ غَفَرْتُ لَكَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2758]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከላቀውና ከተከበረው ጌታቸው ባስተላለፉት (ሐዲሥ) እንዲህ አሉ "አንድ ባሪያ አንድን ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ! " የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም አሁንም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ! የፈለግከውን ስራ በርግጥ ላንተ ምሬሃለሁ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2758]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጌታቸው በሚያወሩት ሐዲሥ አንድ ባሪያ አንድ ወንጀል ሰርቶ ከዚያም "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" ካለ አላህ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀሉን የሚምረው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ብሎ ይሸሽገዋልም ከሱ ይቅር ይለዋልም። ወይም ምሬዋለሁ የሚል ንግግር እንደሚያስከትልለት ነገሩን። ከዚያም ባሪያው በድጋሚ ወንጀል ይሰራና "ጌታዬ ወንጀሌን ማረኝ!" ይላል። አላህም "ባሪያዬ ወንጀልን ሰራ። ለሱ ወንጀልን የሚምር ጌታ እንዳለው አወቀ።" ይልና ይሸሽገዋልም ከሱ ይቅር ይለዋልም። ወይም የሚቀጣውን ቀጥቶ "ለባሪያዬ ምሬዋለሁ" ይላል። ከዚያም ባሪያው በድጋሚ ወንጀል ይሰራና "ጌታዬ ወንጀሌን ማረኝ!" ይላል። አላህም "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምር ጌታ እንዳለው አወቀ!" ይልና ይሸሽገዋልም ከሱ ይቅር ይለዋልም። ወይም የሚቀጣውን ቀጥቶ "ለባሪያዬ ምሬዋለሁ" ይላል። አላህ እንዲህም ይላል: ወንጀልን በሰራ ቁጥር ወንጀሉን በመተውና በመፀፀት ዳግም ወደ ወንጀል ላለመመለስም ቆርጦ እየወሰነ ነገር ግን ነፍሱ እያሸነፈችው ወንጀል ላይ በድጋሚ እየወደቀ በዚህ መልኩ ወንጀል ቢሰራም ተውበት ማድረግን እስካዘወተረ ድረስ የሰራውን ቢሰራ እምረዋለሁ። ተውበት ያለፈውን ወንጀል ታብሳለችና።