عَن أَبِي بُرْدَةَ بْنِ أَبِي مُوسَى رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ:
وَجِعَ أَبُو مُوسَى وَجَعًا شَدِيدًا، فَغُشِيَ عَلَيْهِ وَرَأْسُهُ فِي حَجْرِ امْرَأَةٍ مِنْ أَهْلِهِ، فَلَمْ يَسْتَطِعْ أَنْ يَرُدَّ عَلَيْهَا شَيْئًا، فَلَمَّا أَفَاقَ، قَالَ: أَنَا بَرِيءٌ مِمَّنْ بَرِئَ مِنْهُ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، إِنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بَرِئَ مِنَ الصَّالِقَةِ وَالحَالِقَةِ وَالشَّاقَّةِ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1296]
المزيــد ...
ከአቢ ቡርዳህ ቢን አቢ ሙሳ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
«አቡ ሙሳ ከባድ ህመምን ታመመና ራሱን ሳተ። ጭንቅላቱ ሚስቱ ታፋ ላይ ነበር። (ስታለቅስና ስትገጥም) በርሷ ላይ አንዳችም መልስ መስጠት አልቻለም ነበር። የነቃ ጊዜ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ራሳቸውን ካጠሩት ሰው እኔም የጠራሁ ነኝ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመከራ ወቅት ከምትጮህ፣ ከምትላጭና ልብሷን ከምትቀዳድድ ራሳቸውን አጥርተዋል።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1296]
አቡቡርዳህ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - አባቱ አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከባድ በሽታ እንደታመመና ራሱን እንደሳተ ተናገረ። ጭንቅላቱም ባለቤቱ ታፋ ላይ ነበር። እርሷም እየጮኸች ሙሾ አወረደች። ራሱን ስቶ ስለነበረ አንዳችም ሊመልስላት አልቻለም ነበር። የነቃም ጊዜ እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ራሳቸውን ካጠሩት ሁሉ እኔም አጥርቻለሁ። ነቢዩ: (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከነዚህ ራሳቸውን አጥርተዋል: ከ "ሷሊቃህ": በመከራ ወቅት ድምጿን ከፍ ከምታደርግ፤ ከ "ሓሊቃህ": በመከራ ወቅት ፀጉሯን ከምትላጭ፤ ከ "ሻቃህ": በመከራ ወቅት ልብሷን ከምትቀዳድ የጠራሁ ነኝ ብለዋል። እነዚህ ነገሮች የድንቁርናው ዘመን መገለጫ ስለሆኑ ነው። ይልቁንም በመከራ ወቅት ትእግስት በማድረግና ምንዳውን አላህ ዘንድ በማሰብ አዘዙ።