عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ يُرِدِ اللهُ بِهِ خَيْرًا يُصِبْ مِنْهُ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 5645]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ ለሱ መልካም የሻለትን ሰው ይፈትነዋል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5645]
አላህ በአንድ አማኝ ባሪያው ላይ መልካምን የፈለገ ጊዜ በነፍሳቸው፤ በገንዘባቸውና በቤተሰቦቻቸው እንደሚፈትናቸው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ተናገሩ። ይህም አንድ አማኝ በሱ ምክንያት ወደ አላህ በዱዓእ መጠጋት፣ የወንጀል መማርና የደረጃ ከፍ ማለትን ስለሚያገኝለት ነው።